አዲስ አበባ፤ የካቲት 06/2017(ኢዜአ)፦በአፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ግብርናን በመገንባት ከተረጂነት የተላቀቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር አባል አገራቱ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የአፍሪካ ሕብረት ገለፀ።
ትናንት የተጀመረው 46ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በሁለተኛ ቀን ውሎው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው።
ስብሰባው "የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ይገኛል ።
በህብረቱ የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚና የዘላቂ የአካባቢ ልማት ኮሚሽነር አምባሳደር ጆሴፋ ሳኮ በሰጡት መግለጫ በአፍሪካ ዘመናዊ ግብርና በመገንባት ሕዝቦቿን ከተረጂነት ማላቀቅ ያስፈልጋል ብለዋል።
ድርቅን ጨምሮ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን መቋቋም የሚችል የግብርና አሰራር ለመተግበር የተጀመሩ ሥራዎች ሊጠናከሩ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
በዚህም ኮሚሽኑ የተለያዩ የስትራቴጂ እና የድርጊት መርኃ ግብሮችን ቀርጾ እየተገበረ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በአፍሪካ ከእርዳታ ጥገኝነት የወጣ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁሉም አገራት በትብብር ሊሰሩ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ለዚህ ስኬት ዘላቂ የግብርና ልማት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጣር 2050 የአህጉሪቱ ህዝብ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ይደርሳል ተብሎ መገመቱን ጠቅሰው ለህብረተሰቡ በቂ ምርት ለማቅረብ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግ የግብርና አሰራር መተግበር እንደሚገባ ነው ያስታወቁት፡፡
የግብርና ኢንቨስትመንትን በማሳደግና በፋይናንስ በመደገፍ የዘርፉን ዕድገት ለማሳለጥ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።
በዚህም ግቡን ለማሳካት የሚያስችሉ ሥራዎች መጀመራቸውን ጠቅሰው በአፍሪካ በምግብ ሰብል ራስን ለመቻል የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ ጠቁመዋል።
የምግብና ሥርዓተ ምግብ አጠቃቀምን በማሻሻል ዜጎች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የተጀመሩ ተግባራት ይበልጥ መጠናከር አለባቸው ብለዋል።
በአህጉሪቱ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ በገጠር እንደሚኖርና መተዳደሪያውም በግብርና ላይ የተመሠረተ በመሆኑ አገራት ይህን ታሳቢ ያደረጉ ሥራዎችን ሊሰሩ አንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025