አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ በፀጥታና ደህንነት በኢኮኖሚና በፖለቲካው መስክ የተከናወኑ ተግባራት ሀገር አሻጋሪ መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው አጋማሽ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በመክፈቻ ንግግራቸው፥ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው አጋማሽ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና ሌሎችም መስኮች በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የለውጡ መንግሥት ከተመሠረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የላቁ ተግባራትን ማከናወኑንም ጠቅሰዋል።
በተለይም በፀጥታና ደህንነት በኢኮኖሚና በፖለቲካው መስክ የተከናወኑ ተግባራት ሀገር አሻጋሪ ናቸው ብለዋል።
ብዙ ፈተናዎች ቢገጥሙንም እየተሻገርናቸው ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በቀጣይም ፈተናዎችን ለተሻገረ ድል መትጋት ወሳኝ ነው ብለዋል።
በግማሽ ዓመቱ ከልማት ሥራዎች ባሻገር በርካታ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶችንና ጉባኤዎችን ማስተናገድ መቻሉንም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን ገፅታ የቀየሩና ስሟን በበጎ ያስጠሩ ስራዎች መከናወናቸውን በማንሳት፥ በዓመቱ በዓለም ከፍተኛ የቱሪስት መዳረሻ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ሆናለች ብለዋል።
በድህነትና ኋላቀርነት ትታወቅ የነበረችው ሀገራችን ዓይን ገላጭ ሥራዎችን በመተግበር በበርካታ መስኮች አስደማሚ ለውጥ አምጥታለች ብለዋል።
ለተገኙ ተስፋ ሰጪ ስኬቶች የጠቅላይ ሚኒስትር ተጠሪ ተቋማት የመሪነት ድርሻቸው የላቀ እንደሆነም ገልጸዋል።
የእስካሁን ሥራዎች ጅምር እንጂ የተሟላ የስኬት ደረጃ ላይ አልደረሱም ያሉት አቶ ተመስገን፥ የዓለም ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ ሥራ ከፊታችን ይጠብቀናል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ራሷን እንድትችል እና በአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን የተቀናጀና እረፍት የለሽ ሥራ የግድ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ተጠሪ ተቋማት ከራሳቸው ባለፈ ለሌሎች ተቋማት ግብ መሳካት ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለባቸውም ገልፀዋል።
በተለይ አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን፣ ወጪ ቆጣቢ መሆን፣ ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር እና ተፅዕኖ መፍጠር ላይ ተጠሪ ተቋማቱ የትኩረት ማዕከል መሆን አለባቸው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025