
አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ሩሲያ ጋር ያላቸውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለፁ።
በኢትዮጵያ መንግስት እና በሩሲያ መንግስት የመጀመሪያው የኒውክለር ቴክኖሎጂ ፍኖተ ካርታ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ለመጪዎቹ 3 ዓመታት የሚያገለግል ሁለተኛው ፍኖተ ካርታ በዛሬው ዕለት ተፈርሟል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ እና ሩስያ በኢኮኖሚያዊ ትብብር፣ በባህል ልውውጥ፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና ሽግግር፣ በኢንቨስትመንት፣ በትምህርት፣ በግብርና በንግድ ልውውጥ እና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ዘርፎች ላይ ይበልጥ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

የምክክር መድረኩ ዓላማ የኢትዮጵያና የሩስያ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ከመቼውም በላይ ከፍ በማድረግ የጋራ ስምምነቶችን ለመፍጠር ያለመ ነው።
ከኢትዮጵያ በኩል የኢትዮ-ሩሲያ የበይነ መንግስታቱ የጋራ ኮሚቴ ጣምራ ሰብሳቢ የሆኑት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ከሩሲያ ፌዴሬሽን ጋር የምትጋራውን ለዘመናት ያስቆጠረ እና ታሪካዊ ግንኙነትን ከፍ ለማድረግ እየተደረገ ያለው ጥረት እጅግ ፍሬማ ነው ብለዋል።
ከዚህ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሩሲያ ያደረጉት ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነትን በማጠናከር የጋራ መግባባትና አጋርነት ማሳደጉን ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለው ወዳጅነት የዘመናት ግንኙነት ውጤት ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ የምናከናውናቸው የአጋር ስምምነቶች የዛሬውን አንገብጋቢ ጉዳዮች ከማንሳት ባለፈ ለቀጣይ ትውልዶች ጸንቶ የሚዘልቅና የሚለመልም አጋርነት መሰረት የሚጥል መሆኑን አስገንዝበዋል።

ከሩሲያ በኩል የበይነ_መንግስታት የጋራ ኮሚቴው ጣምራ ሰብሳቢ የሆኑት የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ማክሲም ሬሽቴንኮቭ በበኩላቸው ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት ሰፊ ሰራዎች እየሰራች መሆኑን ጠቁመዋል።
በቀጣይም ግንኙነቱን ይበልጥ በማጠናከርና በመቀራረብ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸውም መግለፃቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በመሆኑም በንግድ፣ በጤና፣ በባንክ ስርዓት፣ በኢነርጂ፣ በቴክኖሎጂ፣ በማስ ሚዲያ፣ በቱሪዝምና ንግድ በሌሎችም ዘርፎች ለመስራት በጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚተጉ አረጋግጠዋል።
በምክክሩ ላይ የጤና፣ የቱሪዝም፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር፣ የትምህርት፣ የውጪ ጉዳይ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና የሌሎች ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026