አዳማ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ልማት ከ16 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ የግብርና ስራው በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለፀ።
በዞኑ በበጋ መስኖ የለማ የስንዴ ምርት መሰብሰብ መጀመሩንም ተገልጿል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ መስፍን ተሾመ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በዞኑ ከአራት ዓመት በፊት የበጋ መስኖ ስንዴ በአንድ ወረዳ በ250 ሄክታር ላይ በሙከራ ደረጃ ነበር የተጀመረው።
በአሁኑ ወቅት በዞኑ በ164 ቀበሌዎች ላይ በ395 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
አርሶ አደሩ የተሻለ ምርት እንዲያገኝ የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ የግብዓት አቅርቦት፣ የሙያ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 16 ነጥብ1 ሚሊዮን ኩንታል ለማግኘት ታቅዷል ነው ያሉት።
ከታረሰው 395 ሺህ ሄክታር ውስጥ እስካሁን 285 ሺህ ሄክታር በዘር መሸፈኑን ገልጸው በክረምት ውሃ የተኛባቸውና አገልግሎት ያልሰጡ መሬቶችን በማልማት የደረሰ የሰብል ምርት እየተሰበሰበ ነው ብለዋል።
እየተሰበሰበ ካለው ምርት በሄክታር ከ70 ኩንታል በላይ እየተገኘ መሆኑን ጠቁመው ምርታማነቱ በአማካይ 40 ኩንታል ላይ መድረሱንም አስረደተዋል።
ከእርሻ ጀምሮ የምርት አሰባሰብ ሂደት ሙሉ በሙሉ በሜካናይዜሽን የታገዘ እንዲሆን በተደረገው ጥረት 85 በመቶ የደረሰው ምርት በኮምባይነር ታግዞ እየተሰበሰበ መሆኑን ገልጸዋል።
አምና አርሶ አደሩ ከሚያገኘው ምርት እንዲቆጥብ በማድረግ 200 ትራክተር ገዝተናል ያሉት ሃላፊው ዘንድሮ በተመሳሳይ 200 ትራክተር አርሶ አደሩ ከሚቆጥበው ለመግዛት ታቅዷል ብለዋል።
በዞኑ 14ሺህ የውሃ መሳቢያ ጀነሬተር አገልግሎት ላይ መሆኑን ጠቅሰው ዘንድሮ ብቻ 2ሺህ 500 የውሃ መሳቢያ ጄኔሬተሮች በብድር ለአርሶ አደሩ ቀርበዋል ብለዋል።
ለሚመረተው ምርትምዩኒየኖች፣ ህብረት ስራ ማህበራትና የዱቄት ፋብሪካዎች ጋር የገበያ ትስስር ተፈጥሯል ሲሉም ገልጸዋል።
የሉሜ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ለሚ ሂርኮ በበኩላቸው፤ በወረዳው በ12 ቀበሌዎች 35 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ በዘር መሸፈኑን ጠቅሰው፤ ቀድሞ የደረሰው ስንዴ ምርት እየተሰበሰበ ነው ብለዋል።
የዘንድሮው የአየር ጠባይ ለበጋ መስኖ አመቺ በመሆኑ ምርቱ ከሚጠበቀው በላይ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
የሉሜ ወረዳ ነዋሪው አርሶ አደር ዳቢ ዓለሙ በሰጡት አስተያየት፤ የዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ሰብል ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የዘንድሮው አየር ጠባይ ጥሩ በመሆኑ አራት ሄክታር መሬት ማልማታቸውን ተናግረው አሁን የስራ ባህል ተለውጦ ማሳ ውስጥ በልማት ላይ ነው የምንውለው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025