ደሴ ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፡ -የአማራ ክልልን ሃብትና ጸጋ በመለየት ለዜጎች የሥራ እድል መፍጠር የሁልጊዜ ተግባራችን ነው ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተሞች ልማት ክላስተር አስተባባሪና የከተማና መሰረት ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር)ገለጹ።
የክልሉ ሥራና ስልጠና ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት አህመዲን መሐመድ(ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ በክልሉ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ የሥራ እድል ፈጠራና የእውቀት ሽግግርን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው።
በዚህም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን ሃብትና ጸጋ በመለየት ለዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል መፍጠር የሁልጊዜ ተግባራችን ነው ብለዋል።
ሰላምና የሥራ እድል የማይነጣጠሉ የክልሉ የትኩረት አጀንዳዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በግማሽ በጀት ዓመቱ በዚህ ተግባር ላይ በመረባረብ አበረታች ውጤት መስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።
በኮደርስ ስልጠና፣ በኮሪደርና ኢንዱስትሪ ልማት ላይ ወጣቱን በማሰማራት በቴክኖሎጂ የበቃና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ለመገንባት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።
የአማራ ክልል ሥራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው(ዶ/ር) በበኩላቸው ፤ በክልሉ የሥራ እድል መፍጠሪያ ፀጋዎችን በመለየት ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅች በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ስልጠና በመስጠት በበጀት ዓመቱ ከታቀደው ውስጥ ባለፉት ሰባት ወራት ከ500 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች በተለያዩ የስራ መስኮች የሥራ እድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል
የብድር፣ የመስሪያና የመሸጫ ቦታ፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር ኢንተርፕራይዞችን ወደ ባለሃብትነት እንዲሸጋገሩና ተጨማሪ የሥራ እድል እንዲፈጥሩ ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በከተማው ለዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ያሉት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድአሚን የሱፍ ናቸው።
ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በሚቆየው መድረክ የክልል፣ የዞን፣ የከተማና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አመራር አባላትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025