
ቦንጋ፤ የካቲት 14/2017(ኢዜአ)፡- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምግብ ዋስትና መርሀ ግብር የታቀፉ ወገኖችን ወደ ምርታማነት በማሸጋገር ለአደጋ የማይበገር ማህበረሰብ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ለማ መሠለ(ዶ/ር) እንዳሉት በክልሉ በምግብ ዋስትና ፕሮጀክት የታቀፉ ወገኖችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር እየተሰራ ነው።
በዚህም ለአደጋ የማይበገር ማህበረሰብ ለመፍጠር የመካከለኛ ጊዜ ስትራቴጂ ዕቅድ ተቀርጾ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በምግብ ዋስትና ፕሮጀክት የታቀፉ 23ሺህ 660 የሚጠጉ ወገኖች በተሰማሩበት የሥራ መስክ በቋሚነት ራሳቸውን የሚችሉበት አቅም እንዲፈጥሩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በፕሮጀክቱ ከታቀፉት ውስጥ በዚህ ዓመት 3ሺህ 170 አባውራዎች በተሰማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ ሆነው እንደሚመረቁ ጠቁመው፣ ቀሪዎቹ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ሙሉ በሙሉ እንደሚመረቁ አክለዋል።
በዚህም የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ አቅም በማሳደግ እርስ በእርስ የሚደጋገፉበትና ምርታማነታቸውን በመጨመር የአደጋ ተጋላጭነትን የሚቋቋሙበት አቅም ለመፍጠር ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል በክልሉ ሊከሰቱ የሚችሉ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል ከሚሰራው ሥራ ጎን ለጎን ለተከሰቱ አደጋዎች በራስ አቅም ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ተናግረዋል።
ማህበረሰቡ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን መቋቋምና በራሱ ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የዳውሮና ኮንታ ዞን አስተዳዳሪዎች ናቸው።

ለተግባራዊነቱም የተረጂነት አመለካከትን በማስቀረት ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ትኩረት መሰጠቱን የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ተናግረዋል።
ከዚህ አንጻር ለሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች የሚያስፈልግ የምግብ አቅርቦት በራስ አቅም መሸፈን የሚያስችል የመጠባበቂያ ክምችት ዞኑ በራሱ አቅም ማጎልበቱን ጠቅስዋል።

የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ በበኩላቸው እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህልን በማጠናከር ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ለአደጋ ጊዜ የሚሆን መጠባበቂያ ሀብት በአይነትና በገንዘብ በማሰባሰብ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ጊዜያዊ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ወደ ምርታማነት ለማሸጋጋር እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026