
ደምቢ ዶሎ፤ የካቲት 14/2017(ኢዜአ)፦ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢው ነዋሪዎች በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ተጠቃሚ እንዲሆን እገዛ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የዩኒቨርሲቲው አስተዳዳር እና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ገመቺስ ብርሃኑ (ዶ/ር) ለኢዜአ አንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የተማረ የሰው ሀብት ከማፍራት በተጓዳኝ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት በትኩረት እያከናወነ ይገኛል፡፡
በተለይም የአካባቢውን ነዋሪ ተጠቃሚ ለማድረግ በትምህርት፣ በግብርናና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋፊ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተለይም የአካባቢው ነዋሪዎች በእንሰሳት፣ በዓሳ እና በአሳማ እርባታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በምርምር የተገኙ የተሻሻሉ ዝርያዎች እያቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።
በቡና፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ እና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች በዩኒቨርሲቲው የምርምር ማዕከሎች የተገኙ የተሻሻሉ ዝርያዎች እየቀረቡ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ዩኒቨርሲቲው በ10 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ የግብርና ስራዎች እያከናወነ መሆኑን አንስተው የአካባቢውን ማህበረሰብ ከማገዝ ባሻገር ዩኒቨርሲቲው በራሱ አቅም ገቢ ለማመንጫት ጥረት እያደረገ መሆኑንም አክለዋል።

በተጨማሪም በቄለም ወለጋ ዞን በኢኒሼቲቭ መልክ የሚተገበረውን የንብ ማነብ ስራ ለማገዝ የተለያዩ ድጋፎች እተቀረበ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።
የደምቦ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ሶሬሳ ሹማ፣ ዩኒቨርስቲው የሚደግፈው የአሳ እርባታ ስራ የአካባቢው ነዋሪ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ እያስቻለ ነው ብለዋል።

ከእንስሳት እርባታ ባሻገር ነዋሪው የአሳ እርባታ ስራን እንዲለማመድ በተደረገው እገዛ ማህበረሰቡ የተመጣጠነ የምግብ እንዲያገኝ እድል መፈጠሩንም ተናግረዋል።
ዩኒቨርስቲው የሚያከናውናቸው የግብርና ምርምር ስራዎች በአካባቢው የሌማት ትሩፋትን ከማገዝ ጎን ለጎን ለወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩንም ገልጸዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026