ቡታጅራ፤ የካቲት 14/2017(ኢዜአ)፡- የቡታጅራ ከተማን ገጽታ የሚቀይርና ለኑሮ ተመራጭ የሚያደርግ የ25 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ ለኢዜአ እንደገለጹት የኮሪደር ልማት ሥራ ከተሞችን ውብ፣ ለኑሮ ምቹና ተወዳዳሪ ለማድረግ ምቹ መደልደል እየፈጠረ ነው።
በቡታጅራ ከተማ በመጀመሪያው ምዕራፍ የግንባታ ሥራ 2 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃቱን ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም በሁለተኛው ምዕራፍ ከተማዋን ምቹና ለኑሮ ተመራጭ የሚያደርግ የ25 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በልማቱ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች እንዲሁም የአረንጓዴና የፋውንቴን ስፍራዎችን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶች መካተታቸውን ጠቁመዋል።
የኮሪደር ልማቱ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተከናወነ ሲሆን አጠቃላይ ሥራውን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት መታቀዱን ገልጸዋል፡፡
ለሥራው የሚያስፈልገው ገንዘብ ከውስጥ ገቢና ህብረተሰቡን በማስተባበርና በማሳተፍ እንደሚሸፈንም አቶ አብዱ አመልክትዋል።
በከተማው የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ ውብና ጽዱ አካባቢ እየፈጠረ መሆኑን የተናገረው ደግሞ የከተማው ነዋሪ ወጣት ጀማል መካ ነው፡፡
እንደወጣቱ ገለጻ ልማቱ ለበርካታ ሰዎች ማረፊያ፣ መዝናኛና ማንበቢያ ስፍራ የፈጠረ ሲሆን ከተማዋንም ለኑሮ ምቹ እያደረጋት በመሆኑ ልማቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
የቡታጅራ ከተማ ነዋሪ አቶ መቻል ታደሰ በበኩላቸው መንግሥት ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና ፅዱ ለማድረግ የጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ የሚበረታታና መጠናከር ያለበት መሆኑን ተናግረዋል።
በከተማው የተከናወነው የኮሪደር ልማት ሥራ ለእግረኛ እና ለተሽከርካሪ መንገዶችን የለየ በመሆኑ የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ ባለፈ የከተማዋን ገጽታ እየቀየረው መሆኑን ጠቁመዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራው የከተማዋን ውበት እየጨመረና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን እያነቃቃ መሆኑን ተናግረው፣ ለሥራው ስኬታማነት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025