የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የንግድ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ ናት - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

Feb 25, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የንግድ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የኢትዮ-ቻይና የ2025 የኢኮኖሚ እና ንግድ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ እንዳሉት፤ የኢትዮ- ቻይና የኢኮኖሚና ንግድ ፎረም የሁለቱን ሀገራት ለማጠናከር ያግዛል፡፡

በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለውን በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማጎልበት ትብብሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ቻይና የኢትዮጵያ ትልቅ የልማት አጋር በመሆኗ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር የጎላ ሚና እንዳላትም ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ኢትዮጵያን ትልቅ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ አጋዥ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል፡፡

በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ኢትዮ-ቴሌኮም እና የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጋቸውንም አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም የዲጂታል ፋይናንስና ቴክኖሎጂ እድገት የኢትዮጵያን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ መጠቀም የሚቻልበት ጊዜ አሁን መሆኑን ያመላክታሉ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የንግድ ትስስርን ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸው፤ የቻይና ካምፓኒዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት እድሎችን እንዲጠቀሙ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ኢትዮጵያ በተፈጥሯዊ እና በባህላዊ ሀብቶች የታደለች ሀገር መሆኗን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እና ቻይና የላቀ የንግድና ኢንቨስትመንት አጋሮች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ተጨማሪ የትብብር አቅምን ያሳድጋል ብለዋል።

የዲጂታል ኢኮኖሚ፣ ግብርና እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ይበልጥ ተጠናክሮ የሚሰራባቸው የትብብር መስኮች መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር)፣ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ አካታችና ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በአይ ሲ ቲ፣ በቱሪዝም እና ግብርና እንዲሁም በማዕድን ዘርፎች ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዳሏት ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ያለው የኢኮኖሚ ትብብር ፈጣን እድገት ላይ መሆኑን ገልጸው፤ የቻይና ባለሀብቶች እድሉን አጠናክረው ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል።

በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሰማራት ለሚፈልጉ ኢንቨስተሮች የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡

የቻይና ዓለም አቀፍ ንግድ ማስታወቂያ ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ቼን ጂያንአን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካና በቀጣናው ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆኗን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ያለው ሁሉን አቀፍ ትብብር ትልቅ እድገት እያሳየ መምጣቱንም ገልጸዋል።

በአፍሪካ ፈጣን እድገት የምታስመዘግብ፣ ለሮድ ኤንድ ቤልት ኢኒሼቲቭ ውጤታማነት የጎላ ሚና ያላትና የቻይና ወሳኝ አጋር መሆኗንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025