ደብረ ብርሃን፤ የካቲት 18/ 2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፍ አብዮት እየፈጠረ መምጣቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።
ሚኒስቴሩ በደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ምርት የተሸጋገሩ አምስት ኢንዱስትሪዎችን መርቀዋል።
በዚሁ ወቅት እንዳሉትም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ እንደ ሀገር ከፍተኛ ለውጥ ተመዝግቧል።
የንቅናቄው መጀመር ወደ ግንባታ ያልገቡት ኢንዱስትሪዎች ወደ ግንባታ እንዲገቡ እና ምርት ያልጀመሩት ደግሞ ወደ ማምረት እንዲገቡ አስችሏል።
በአገር በቀል ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የሰጠው ልዩ ትኩረት ውጤት እንደሆነም ጠቁመዋል።
በደብረ ብርሃን ከተማ የኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴ ክልሉ የኢንዱስትሪ ስበት ማዕከል ለመሆን ያለውን ጥረት ማሳያ ነው ብለዋል።
የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በበኩላቸው በክልሉ በዚህ ዓመት ብቻ 111 በላይ ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት ተሸጋግረዋል።
ክልሉ የማዕድን፣ የቱሪዝም፣ የግብርና፣ የአግሮ ፕሮሰሲንግና ሌሎች ሃብቶች ባለቤት በመሆኑ በቀጣይም ያለውን ጸጋ ተጠቅሞ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንዳሉት ባለፉት ሶስት ዓመታት 56 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ያስመዘገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ከተማው ማምጣት ተችሏል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ የባለሀብቱና የመንግስት ግንኙነት እየተጠናከረ መጥቷል ያሉት አቶ በድሉ፤ ባለፉት ሰባት ወራት ከ120 በላይ ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ጥያቄ አቅርበው እየታየ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ያልተሸጋገሩ ስምንት ባለሃብቶች የተሰጣቸው መሬት መነጠቁን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025