
አዲስ አበባ ፤ የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል የመሆን እቅዷን ለማሳካት እየሰራች መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ለአምስተኛው የዓለም የንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ የቴክኒክ ኮሚቴ የመጨረሻ ዝግጅት ላይ ተገኝተን የስራ አቅጣጫ ሰተናል ሲሉ አስፍረዋል።
የቴክኒክ ኮሚቴው በቢሾፍቱ በማካሄድ ላይ በሚገኘው ዝግጅት እ.አ.አ በ2026 በካሜሮን ለሚካሄደው የአለም ንግድ ድርጅት 14ኛው የሚኒስትሮች ኮንፍረንስ ላይ የኢትዮጵያን አባልነት ለማሳካት ያለመ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።
በዚህ መሰረት በከፍተኛ ሞራል፣ የሃገር ፍቅርና በሙያ ብቃት ዝግጅት ማድረግና ለተደራዳሪ ቡድኑ አቅም መሆን እንዳለባቸው መግለጻቸውን በጽሑፋቸው አስፍረዋል።
የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ንጎዚ ኦኮንጆ በቅርቡ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026