ባህርዳር፤ የካቲት 18/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የሚካሄደውን ሰላምና ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል ፍትሃዊ የሆነ የግብር አስተዳደር ለማስፈን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ።
በክልሉ ገቢዎች ቢሮና በፌደራል ገቢዎች ሚኒስቴር የጋራ ትብብር "ግብር፣ ለሀገር ክብር" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ የግብር የንቅናቄ መድረክ በባህር ዳር ከተማ ዛሬ ተካሄዷል።
ርእሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ላይ እንዳሉት በክልሉ ሀብት በማፍራት በማከማቸትና አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመፍጠር ላይ በማተኮር መስራት ይገባል።
ለክልሉ ሰላምና ልማት የሚያስፈልገውን ገቢ ለመሰብሰብና ጥቅም ላይ ለማዋል በሃብት ፈጠራ ማከማቸትና ኢንቨስት ማድረግ ላይ በትኩረት መሰራት ያለበት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ለዚህም በክልሉ ፍትሃዊ የግብር አስተዳደርን በማስፈን የተረጋጋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ማጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል።
በክልሉ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ሃብት በማፍራት ከሚያገኙት ገቢ የሚጠበቅባቸውን ግብር የሚከፍሉ ምስጉን ባለሃብቶችን ማበረታታት እንደሚገባም ገልጸዋል።
በተጨማሪም የክልሉ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ እንዲቻል የግብር አስተዳደር ህጉን በአግባቡ መተግበር እንደሚገባም አስረድተዋል።
የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ በበኩላቸው የዜጎችን የልማት ፍላጎት ተደራሽ ለማድረግና ሰላምን ለማረጋገጥ ግብርን በአግባቡ መሰብሰብና መምራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የሀገራችንን ተጽዕኖ ፈጣሪነት ደረጃ በደረጃ ለማሻሻል በራስ አቅም የተመሰረተ ኢኮኖሚን መገንባት አስፈላጊ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ይህም አገራችን ያላትን የመልማትና የማደግ አቅም ለመጠቀም ያስችላል ብለዋል።
የአገሪቱ የታክስ አሰባሰብ ስርዓት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ ቢሆንም ከሌሎች የሰሃራ በታች አገራት ጋር ሲነጻጸር አሁንም ሰፊ ስራ የሚጠይቅ መሆኑን አስረድተዋል።
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብረት ማሕመድ በበኩላቸው ከአገራዊ ሪፎርሙ ወዲህ የክልሉ ግብር የመሰብሰብ አቅም በአራት እጥፍ ማደግ እንደቻለ ገልጸው ክልሉ ካለው ሁሉን አቀፍ ጸጋና ሃብት አንጻር ሲታይ ግን አሁንም የሚቀረው ጉዳይ መኖሩን አስረድተዋል።
በክልሉ ባለፉት ሰባት ወራት የተሰበሰበው 31 ቢሊዮን ብር ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የአስር ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው መሆኑንም አስረድተዋል።
በንቅናቄ መድረኩ ላይም ለምስጉን ግብር ከፋዮች ለተባባሪ ተቋማትና ውጤታማ ለሆኑ በየደረጃው ለሚገኙ ገቢ ሰብሳቢ ሰራተኞች እውቅና ተሰጥቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025