
ሀዋሳ፤ የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል እየተከናወነ ያለው የመስኖ ልማት ገበያ በማረጋጋትና በስራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ ሚና እየተጫወተ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ ምክር ቤት አባላት አሳሰቡ፡፡
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አባላት በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን እና በሃዋሳ ከተማ የተከናወኑ የመስኖ እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል፡፡
በምልከታቸውም የመስኖ ልማት ስራዎች ገበያን ማረጋጋት እና ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር ያላቸውን ጉልህ ሚና ገልጸዋል።
ከምክር ቤት አባላት መካከል አቶ ሚሊዮን ዮሳ እና ወይዘሮ ኤልሳቤት ፍቼ ለኢዜአ እንዳሉት በግብርናው መስክ የልማት ስራዎች የህዝቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው።
ለአብነትም መስኖ ልማቱ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚን ለማሳደግና የስራ ዕድል ለመፍጠር ያለውን ጉልህ ሚና አንስተዋል።
ጦም ያደረ ሰፊ መሬትን በመስኖ ማልማት ምርታማነትን መጨመር መቻሉን ጠቅሰው፤ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በማስፋት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
አቶ ታረቀኝ ታምሬ በበኩላቸው የግብርና ልማቱ የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚ አቅም የሚያሳድግና የህዝቡን ኑሮ የሚያረጋጋ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የተጀመሩ የመስኖ ልማት ስራዎች በቀጣይነት እንዲስፋፉ ምክር ቤቱ ክትትሉን እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል።
የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ዘነበ ዘርፉ፤ የምክር ቤት አባላቱ በሁለት ቡድን በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችና በሃዋሳ ከተማ የመስክ ምልከታ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
የምክር ቤት አባላቱ ከሪፖርት ባለፈ በተጨባጭ የተሰሩ ስራዎችን በመስክ ምልከታ ለማረጋገጥ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
የተጀመሩ የልማት ስራዎች በሁሉም አካባቢዎች እንዲስፋፉና ቀጣይነት እንዲኖራቸው ምክር ቤቱ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባዔውን ነገ ይጀምራል።፡
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026