አዳማ ፤ የካቲት 20/2017( ኢዜአ)፦ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የልህቀት ማዕከላቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማደራጀት የሚያስችለውን ስምምነት ከደቡብ ኮሪያው ሳምሳንግ ኩባንያ ጋር ዛሬ ተፈራረመ።
የልህቀት ማዕከላቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መደራጀት የሀገሪቷን የኢንዱስትሪ ልማት በዘመናዊ የምርምር ቴክኖሎጂ ውጤቶችና ግኝቶች ለመደገፍ እንደሚያስችለው ተገልጿል።
የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ፣ ፋርማሲዩቲካል፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ አድቫንስ ማኑፋክቸሪንግና አድቫንስ ማቴሪያል ደግሞ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲደራጁ አምስቱ የዩኒቨርሲቲው የልህቀት ማዕከላት መሆናቸው ታውቋል።
ለእነዚህ የልህቀት ማዕከላት ዘመኑ የደረሰበትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማሟላት የሚያስችለው ስምምነት ነው ከደቡብ ኮሪያው የሰምሳንግ ቴክኖሎጂ ኩባንያና ኮንሰርቲየም ጋር ዛሬ የተፈራረሙት።
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለፁት የልህቀት ማዕከላቱን የምርምር ፓርክ አሁን የዓለም የምርምር ቴክኖሎጂ ደረጃ በደረሰበት የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ለማደራጀት የዛሬው ስምምነት ተፈርሟል።
''የላቦራቶሪ ግብዓቱ ግዥ በረዥም ጊዜ ብድር ከደቡብ ኮሪያ በተገኘው 100 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከሰምሳንግ ኩባንያ ጋር ተፈራርመናል'' ብለዋል።
በኩባንያው በኩል የምርምር ላቦራቶሪ መሳሪያዎችን የመገጣጠም ስራ በአንድ ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል።
የሳምሰንግ ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኮርፖሬሽን የምስራቅ አፍሪካ ስራ አስኪያጅ ቹልሱን ሀዋንግ በበኩላቸው ኩባንያው የላብራቶሪ ቴክኖሎጂዎችና የምርምር መሳሪያዎችን በቅርቡ የማደራጀት ስራ ይጀመራል ብለዋል።
የልህቀት ማዕከላቱ የምርምር ቴክኖሎጂዎችን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የማደራጀት ስራውን እንደሚያጠናቀቅም ገልጸዋል።
ኩባንያው ከመሳሪያዎች መገጣጣም ባሻገር የመብራት፣ ውሃ፣ የውስጥ መስመሮች እና የላቦራቶሪ ማስተዳደር የሚያግዙ ሶፍትዌሮች እንደሚያለማ ተገልጿል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025