
ሀዋሳ የካቲት 24/2017 (ኢዜአ) :- በሲዳማ ክልል አምራች ኢንዱስትሪውን በመደገፍ ዘርፉ የሚያስገኘውን ጥቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በክልሉ በሀዋሳ ከተማ በግል ባለሀብት በ80 ሚሊየን ብር የተገነባ የእብነበረድና ግራናይት ፋብሪካ ተመርቆ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና በዚህ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ የይርጋለምና ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉትን ጨምሮ ከ1 ሺህ 300 በላይ ኢንዱስትሪዎች ይገኛሉ፡፡
በክልሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ ዘርፉ የሚያስገኘውን ጥቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ ያለው ሰላምና ለአምራች ኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆን የጥሬ እቃ አቅርቦት መኖር ዘርፉን የሚቀላቀሉ ባለሃብቶችን ቁጥር እያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለአብነት የዛሬውን ጨምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከአምስት በላይ አምራች ኢንደስትሪዎች ወደ ስራ መግባታቸውን አንስተው ይህም የክልሉን ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለመደገፍ አዲስ ፖሊሲ ቀርጾ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
"ፖሊሲው የግል ባለሃብቶች ዘርፉን እንዲቀላቀሉና መሪ ተዋናይ እንዲሆኑ የሚያደርግ በመሆኑ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማነት የተቀናጀ ድጋፍ ያስፈልጋል "ብለዋል፡፡
መንግስት ለአምራች ዘርፉ የሚሰጠውን የፋይናንስ ድጋፍ ለማሳደግ የፖሊሲ አቅጣጫ ማስቀመጡን ገልጸው የግል ባለሃብቶች ያለውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው በሀገር እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
ፋብሪካው በ80 ሚሊዮን ብር ካፒታል ወደ ስራ መግባቱን የገለጹት የዓለም እብነበረድና ግራናይት ፋብሪካ ባለቤት አቶ ዓለምገና ዘርጋው በበኩላቸው "ለ80 ሰዎች የስራ እድል የሚፈጥር ነው" ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግስት ቦታ ከመስጠት ጀምሮ ለፋብሪካው ግብዓት የሚሆኑ እብነበረድና ግራናይት ሃብቶችን በጥናት በመለየት እገዛ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከፋብሪካው በሚገኘው ተረፈ ምርት የሳሙናና ቀለም ፋብሪካ የማቋቋም እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
በፋብሪካው የስራ እድል የተፈጠረለት ወጣት ውብሸት በቀለ በማሽን ኦፕሬተርነት እየሰራ መሆኑን ጠቅሶ ክህሎቱን የሚያሳድግበት ስልጠና መውሰዱንም ተናግሯል፡፡
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026