አዳማ፤ የካቲት 30/2017 ዓ.ም (ኢዜአ)፦ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የተቀናጀና የተናበበ መረጃን ተደራሽ ማድረግ እንዲችል ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለፁ።
የፌዴራልና የክልል መንግስት ኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ተቋማት ሃላፊዎች ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ መድረኩ ዘርፉን ለማጠናከር የተሻለ አቅም የተፈጠረበት ነው።
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት ዓላማ መር፣ የተቀናጀ እና የተናበበ መረጃን ተደራሽ ማድረግ የሚያስችላቸው ገለጻ በመድረኩ መደረጉን ተናግረዋል።
ይህም ዘርፉ እርስ በርስ የሚደጋገፍበት፣ የተቀናጀ የመረጃ ፍሰት ስርዓት እንዲኖር እና የጋራ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ወጥ መልእክቶችን ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
ዘርፉ የሚናገር ብቻ ሳይሆን ሕብረ ብሔረዊ አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም የብሔራዊነት ትርክትን ለመገንባት ትልቅ አስተዋጾ እንዲኖረው ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ ረገድ ሚኒስቴሩ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ አስራርና ስታንዳርዶችን በማዘጋጀትና ተፈጻሚነታቸውን በመከታተል የተቀናጀና የተናበበ መረጃ ተደራሽ እንዲሆን በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ከሚዲያ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያጠናከር አስፈላጊ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑን አቶ ተስፋሁን አክለዋል።
እንደ ሚኒስትር ደኤታ ገለጻ ባለንበት ዲጂታል ዓለም ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ዘርፉ የበለጠ አቅሙን ማጠናከር እንዳለበት በመድረኩ አቅጣጫ ተቀምጧል።
የሚዲያ እና ኮሚነኬሽን ዘርፉ ሀሰተኛ መረጃን ከመመከት አንጻር ትክክለኛ መረጃን በተከታታይ ተደራሽ ማድረግ ላይ ሊያተኩር ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።
የግምገማ መድረኩ ተሳታፊዎች በአዳማ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን የጎበኙ ሲሆን ጉብኝቱም ልምድ የሚወሰድበት መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይ የአዳማ ከተማን ስማርት ሲቲ በማድረግ በኩል እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ይህም ከአገልግሎት አሰጣጥ አንጻር ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በአዳማ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የከተማ ግብርና ሥራዎች የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርን ለማሳካት የሚያግዙ መሆናቸውን ተሳታፊዎች ጠቅሰዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025