
መተማ፤ የካቲት 29/2017(ኢዜአ)፡- በምዕራብ ጎንደር ዞን ከመስኖ ልማት ከ428 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
በገንዳውኃ ከተማ የአንደኛ ዙር የበጋ መስኖ ልማት ስራ አፈጻጸም ግምገማና የ2ኛ ዙር የመስኖ ልማትን በተመለከተ ጉብኝት ተካሂዷል።
በምዕራብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ጤናው ፈንታሁን፤ በዞኑ በአንደኛ ዙር የመስኖ ልማት ከ4 ሺህ 500 በላይ አርሶ አደሮች የተሳተፉበት 2 ሺህ 500 ሄክታር መሬት መልማቱን ገልጸዋል።
ከዚህም ከ428 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን በሁለተኛው ዙርም ከታቀደው በላይ ለማሳካት የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል።
የተገኘው ምርት ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው የገበያ ችግር እንዳይከሰትም ከንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ጋር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የዛሬው ጉብኝት ዓላማም የአርሶ አደሮቹን የምርት ሁኔታ በመገምገም የገበያ ትስስሩን ለማቀላጠፍ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
ከመስኖ አምራች አርሶአደሮች መካከል አቶ ጥላሁን የሱፍ፤ ከአራት ሄክታር በላይ መሬታቸውን በመስኖ በማልማት ከ500 ኩንታል በላይ ምርት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ዘንድሮ የግብአት አቅርቦቱ የተሻለ በመሆኑ ከጠበቁት ባላይ የአትክልት ምርት ማግኘታቸውን ጠቁመውየገበያ ትስስሩ ቀድሞ ባለመፈጠሩ ከሽያጩ ያገኙት ገቢ የምርቱን ያህል አለመሆኑን ተናግረዋል።
ሌላኛው አልሚ አርሶ አደር ሀሰን አልዩ፤ በሶስት ሄክታር መሬት ላይ ካለሙት ሰብል ከ400 ኩንታል በላይ ምርት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
በመስኖ ልማቱ ለአራት ሰዎች የስራ እድል መፍጠራቸውን ጠቅሰው የገበያ ትስስሩ ፈጥኖ ካልተፈጠረላቸው ለኪሳራ እዳረጋለሁ የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል።
በስድስት ሄክታር መሬት ላይ አትክልት እያለሙ ያሉት አርሶ አደር ማማር ሙሉጌታ፤ የተገኘው ምርት ከፍተኛ በመሆኑ የገበያ ትስስር ይፈጠርልን ሲሉ ጠይቀዋል።
በዞኑ በ2ኛው ዙር የመስኖ ልማት ከ550 ሄክታር መሬት በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ እስካሁን 138 ሄክታር ማልማት መቻሉ ታውቋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026