
ባህርዳር የካቲት 29/2017 (ኢዜአ) በባህርዳር ከተማ የሌማት ትሩፋትን ጨምሮ በተለያዩ የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ሴቶች ውጤታማ መሆናቸውን ገለፁ።
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ‘‘ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ አገልግሎት በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል’’ በሚል መሪ ሃሳብ የስኬታማ ሴቶች የስራ እንቅስቃሴ በባህርዳር ከተማ ምልከታ ተደርጎበታል።
ገነት፣ ዮሴፍና ጓደኞቻቸው የህብረት ሽርክና ማህበር ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ገነት አበባው እንደገለጹት በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በዶሮና አሳን በኩሬ በማርባት ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ሆነዋል።
ሴቶቹ በአካባቢው ባልተለመደ መልኩ አሳን በኩሬ ከማርባት ጀምሮ የፍራፍሬ ምርቶችን ለገበያ እስከማቅረብ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ከራሳቸው ፍጆታ የተረፈን ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ጥቅል ጎመን፣ ሰላጣና ሌሎች የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንደሆኑም አብራርተዋል።
የአብስራ ሁለገብ ፋሽንና ዲዛይን ባለቤት ወይዘሮ እናኑ ደሴ እንደገለፁት በተደረገላቸው የገንዘብና የመስሪያ ቦታ ድጋፍ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም በልብስ ስፌትና በጫማ ስራ ተሰማርተዋል።
በተጨማሪም አሁን ላይ የተለያዩ የልብስ አይነቶችን ሰፍቶ በማቅረብና ጫማዎችን በማምረት ዘርፍ ላይም ተሰማርተው ውጤታማነታቸውን እንዳረጋገጡም ገልፀዋል።
በዶሮ እርባታ ዘርፍ የተሰማሩት ወይዘሮ እመቤት በዛብህ በበኩላቸው ከአንድ ዓመት በፊት በመኖሪያ ቤታቸው በ50 እንቁላል ጣይ ዶሮዎች የጀመሩትን ስራ አሁን ላይ ወደ 250 ማሳደግ እንደቻሉ ገልጸዋል።

የባህርዳር ከተማ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ሰብለ ዘውዱ በበኩላቸው የዘንድሮው የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን አከባበር ለየት የሚያደርገው የተለወጡ ሴቶችን በመጎብኘትና በማበረታታት በመሆኑ ነው ብለዋል።
በሌማት ትሩፋትና በሌሎችም የስራ መስኮች የተሰማሩ ሴቶችን በብድር፣ በመስሪያና በመሸጫ ቦታ መደገፍ ከተቻለ ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ተላቀው ለሌሎች ሞዴል እንደሚሆኑ ከጉብኝቱ መገንዘባቸውን ተናግረዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ሴቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ እሌኒ አባይ በበኩላቸው በዶሮና በዓሳ እርባታ፣ በጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በልብስ ስፌትና በጫማ ስራ የተሰማሩ ሴቶች ያሳዩት ለውጥ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።
ይህም ሴቶችን መደገፍና ማበረታታት ከተቻለ ራሳቸውን ከመቻል አልፈው ለሌሎች የስራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚው መሪ ተዋናይ ከመሆን የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ ጉብኝቱ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመስክ ጉብኝቱም የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ ሴት የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026