
አሶሳ፤ መጋቢት 01/2017(ኢዜአ):- የአካባቢው ማህበረሰብ የሥራ ባህል እንዲቀየርና በሀብቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ድጋፍ የሚያደርጉ መሆናቸውን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የዳቡስ ወንዝን በመጠቀም በመስኖ እያለማ ያለው ድርጅት ገለጸ።
በክልሉ ኡንዱሉ ወረዳ በእርሻና መስኖ ልማት የተሰማራው የሮኤል የተቀናጀ እርሻና መስኖ ልማት ድርጅት የዳቡስ ወንዝን በመጠቀም የመስኖ ስራ እያከናወነ መሆኑን ነው የገለጸው።
የድርጅቱ ምክትል ማናጀር አቶ ማንእንደራስ ይንገስ እንዳሉት፤ ድርጅቱ የልማት ስራውን የጀመረው ከአራት ወራት በፊት ሲሆን በአሁኑ ወቅት አስር ሄክታር ማሳ ላይ ቲማቲም፣ ሽንኩርት እና ሀባብ እያለማ ይገኛል።
እየለማ ካለው አምስት ሄክታር የቲማቲም ማሳ ላይ እስከ 7 ሺህ 500 ኩንታል ምርት እንደሚጠብቁ ገልጸው፤ በቀጣይ በፍራፍሬ ምርቶች ላይ በስፋት ለመስራት የማሳ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በተለይም ቤኒሻንጉል የሚታወቅበት የማንጎ ምርት ትልቁ እቅዳቸው መሆኑን አንስተዋል።
የዳቡስ ወንዝ በአካባቢው ያለው ለም አፈር ለመስኖ ልማት ስራቸው አመቺ በመሆኑ በልማቱ ውጤታማ እንደሚሆኑ ተስፋ ሰንቀዋል።
ድርጅቱ በእንስሳት እና ንብ እርባታ ለመሰማራት ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ 200 ፍየሎችን እንደሚያስገቡም ተናግረዋል።
የአካባቢው ማህበረሰብ የስራ ባህል እንዲቀየር እና ህብረተሰቡ ምርቱን በአቅራቢያው እንዲያኝ ማድረግ የድርጅቱ ዓላማ እንደሆነም አብራርተዋል።
ድርጅቱ 80 ለሚደርሱ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችም የድርጅቱን የሥራ እንቅሰቃሴ እንደሚከታተሉት ምክትል ማናጀሩ አስታውቀዋል።
የስራ ዕድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶች መካከል ወጣት ገብረእግዚአብሔር ገብረእየሱስ እንደተናገረው በድርጅቱ በሚያገኘው ገቢ እራሱን እያስተዳደረ ነው።

ከዓረብ አገር ስደት መልስ በአገር ቤት የጀመረው ሥራ በመሆኑም ጥሩ አየር እየተነፈሰና እድገትን ሰንቆ በመስራት ላይ መሆኑን ተናግሯል።
ድርጅቱ በርካታ ባለሙያዎችን የያዘ መሆኑን የገለጸው ወጣቱ የተለያዩ ሙያዎችን እየተማሩ እንደሆነም ገልጿል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026