የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎችን በማላመድ አረንጓዴ ልማትን መገንባት ይገባል

Mar 12, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፦የኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎችን በማላመድ አረንጓዴ ልማትን ለመገንባት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ገለፁ።


በኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች ማስፈፀሚያ ረቂቅ ስትራቴጂ ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።


ስትራቴጂውን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በጋራ እንዳዘጋጁት በመድረኩ ተገልጿል፡፡


በውይይቱ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ ሚኒስትር ዴኤታዎችና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።


በዚሁ ወቅት የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።


የትራንስፖርት ዘርፉ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ለስኬታማነቱ ዘርፉን የታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነም ጠቅሰዋል።


ታዳሽ ሃይል የአየር ብክለትን ከመቀነስ ባለፈ ለነዳጅ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታ ለማዋል ያስችላል ነው ያሉት።


ከተሞችን ፅዱና ስማርት ለማድረግ የጎላ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፥ ለዚህ ደግሞ የኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎችን ማስፋፋት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡


ይህን ለማሳካት የሁሉንም ቅንጅት የሚጠይቅ ነው ብለዋል።


መድረኩ የኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች ማስፈፀሚያ ረቂቅ ስትራቴጂ ላይ ከመወያየት ባለፈ ወደ ተጨባጭ ስራ ለመግባት የሚያስችል መሆኑንም አስታውቀዋል።


በዚህም ታዳሽ ኃይል የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን በስፋት ስራ ላይ ለማዋል የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025