አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፡- በሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ልማት ላይ የሚያጋጥመውን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመፍታት ከፋይናንስ ተቋማት ጋር የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአዋሽ ባንክ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።
ለአምስት አመታት የሚቆየውን ስምምነት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጸሐይ ሽፈራው ጋር ተፈራርመዋል።
ተቋማቱ የሠራተኞች አቅምን ለመገንባት፣ የዲጂታል ኢንተርፕራይዞች እድገትን ለማፋጠንና የሥራ ፈጠራ ስልጠናን ለማበረታታት በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት በሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ማጎልበት ላይ የሚያጋጥመውን የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት ለመፍታት ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
ስምምነቱ የፋይናንስ አቅርቦትን በማመቻቸትና ኢንተርፕራይዞችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ በርካታ ዜጎችን ወደ ሥራ ለማስገባት ያግዛል ብለዋል።
ሚኒስቴሩ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ አስር ሚሊየን ለሚጠጉ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠሩን አስታውቀዋል።
ኢንተርፕራይዞቹ ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ተኪ ምርቶችን በማምረት ለሀገሪቱ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የስራ ገበያን መሰረት በማድረግ እየተሰሩ ባሉ ሥራዎች ጥራት ያለው የሰው ሃይል ማፍራት መቻሉን ነው ያስረዱት።
በተቋሙ የተጀመሩ ሥራዎችን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።
የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጸሐይ ሽፈራው በበኩላቸው ባንኩ በዚህ ዓመት ከ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለአነስተኛ እና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች መስጠቱን ገልጸዋል።
በተጨማሪም አካታች የፋይናንስ ስርዓት እንዲኖር ለአርሶና አርብቶ አደሩ ብድር እያቀረበ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025