ጎንደር፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፡- የጎንደር ከተማ ነዋሪ የኮሪደር ልማት ስራውን በመደገፍ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት አስተዋጽኦ ማበርከቱን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በልማትና በሰላም ዙሪያ ዛሬ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ ታደሰ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በበጀት ዓመቱ በከተማው ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
ፕሮጀክቶቹም 6 አዳዲስና 13 ነባር እንደሆኑ አመልክተዋል።
የከተማው ህዝብም ለኮሪደር ልማቱ የራሱን ህንጻና መኖሪያ ቤት በማደስ እና መብራት በመዘርጋት ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የጎንደር ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋ መኮንን በበኩላቸው፤ ህዝባዊ የውይይት መድረኮች
በከተማ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና በርካታ የልማት ስራዎችን ለማከናወን ማስቻላቸውን አስረድተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃኑ ጣምያለው፤ የክልሉ መንግስት ከተሞችን ጽዱ፣ አረንጓዴና ለነዋሪዎች ምቹ የማድረግ ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለከተሞች ልማትና እድገት መፋጠን በመንግስት በኩል ከፍተኛ ቁርጠኝነት መኖሩን ጠቅሰው፤ ተስፋ ሰጪ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለአብነትም በጎንደር ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት በኮሪደርና በሌሎችም ዘርፎች የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን አጠናክሮ በመቀጠል በላቀ ደረጃ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰላም ፀንቶ እንዲዘልቅ ህብረተሰቡ ድጋፉንና ተሳትፎውን እንዲያጠናከር መልዕክት አስተላለፈዋል፡፡
ከመድረኩ ተሳታዎች መካከል አቶ አላምረው ጸጋው በሰጡት አስተያየት በከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተጨባጭ ምላሽ የሰጡ ናቸው ብለዋል፡፡
ወይዘሮ ብርቱካን አለምነው በበኩላቸው፤ ልማትና ሰላም የማይነጣጠሉ በመሆናቸው የከተማውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር አባላት፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ምሁራን ተሳትፈዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025