
ገንዳ ውሃ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፡- ዩኒዬኖችንና የሕብረት ሥራ ማህበራትን በማጠናከር በገበያ ማረጋጋት ሥራ የድርሻቸውን እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ገልጸ።
መተማ የገበሬዎች ሁለገብ ዩኒዬን ከ8 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ያቀረባቸውን መሰረታዊ ሸቀጦች ዛሬ ለሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት አከፋፍሏል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ህብረት ሥራ ማህበራት ተጠሪ ጽህፈት ኃላፊ ወይዘሮ በልጣ ጌትነት በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ በዞኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጉዳት ለመቀነስ እየተሰራ ነው።
ዩኒዬኖችንና የህብረት ሥራ ማህበራትን በማጠናከር የግብርናና የፋብሪካ የፍጆታ ምርቶችን ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

ለዚህም በወረዳና በከተሞች ለሸማች ሕብረት ሥራ ማህበራት ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ተዘዋዋሪ ብድር ለመስጠት ታቅዶ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ጥቅም ላይ መዋሉን ነው የገለጹት።
ከ2ሺህ ኩንታል በላይ ማሽላ፣ ከ500 ኩንታል በላይ ጤፍ፣ ከ10 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት፣ ከ800 ኩንታል በላይ ስኳርና ሌሎች ምርቶች ለሸማቹ መከፋፈላቸውን አስረድተዋል።

የመተማ ገበሬዎች ሁለገብ ዩኒዮን ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብቴ ዘውዱ በበኩላቸው፣ ዛሬ ለሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት የተከፋፈሉት ከ8 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 10ሺህ ሊትር ዘይት፣ 100 ኩንታል የዳቦ ዱቄት እና 469 ኩንታል ስኳር ናቸው።
ዩኒየኑ በገበያ ማረጋጋት ተግባር የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልፀው፣ ከ6ሺህ ኩንታል በላይ የግብርና ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ መሆኑንም ተናግረዋል።
ይህን ተግባሩን በቀጣይም አጠናክሮ ለማስቀጠል ያቀረቡት 40 ሚሊዮን ብር ብድር መፈቀዱንም አመልክተዋል

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እያሱ ይላቅ በበኩላቸው ሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ባላቸው ሀብት የፍጆታ እቃዎችን በማስመጣት ለህብረተሰቡ ማከፋፈል እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት እያከናወኑት ያለው ገበያን የማረጋጋት ሥራ ያለአግባብ ለመክበር የዋጋ ጭማሬ የሚያደርጉ ስግብግብ ነጋዴዎችን እንቅስቃሴ ይገታል ብለዋል።
የዞኑ አስተዳደር ገበያው እንዲረጋጋ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከሚሰራው ሥራ በተጨማሪ የህብረት ሥራ ማህበራትን የመደገፍ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በምዕራብ ጎንደር ዞን 119 ሕብረት ሥራ ማህበራት እና ሁለት ዩኒየኖች እንዳሉ ታውቋል።
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...
Jun 9, 2026
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...
Jun 6, 2026
ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያ...
May 28, 2026