ሀዋሳ፤ መጋቢት 6/2017(ኢዜአ)--በሲዳማ ክልል የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት በሥራ ዕድል ፈጠራ የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራ የክልሉ ሥራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አስታወቀ።
በክልሉ በበጀት ዓመቱ ያለፉት ስምንት ወራት ከ44 ሺህ ለሚበልጡ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩም ተመላክቷል።
በሀዋሳ ከተማ የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶች ጋር ቢሮው ዛሬ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በውይይት ላይ የተገኙት የቢሮው ሃላፊዋ ወይዘሮ ሀገረጽዮን አበበ እንደገለጹት በክልሉ በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የታየው የአመለካከት ለውጥ ውጤት እያስገኘ ነው።
የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን በማሳደግ ሀብት ከማፍራት ባለፈ ለሌሎችም የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ተናግረዋል።
ወጣቶች ያላቸውን አማራጭና ጊዜያቸውን በአግባቡ ተጠቅመው ለስኬት እንዲበቁም የህይወት ክህሎት ስልጠና እንደሚሰጣቸውም ገልጸዋል።
የቢሮው ምክትልና የሥራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ከፍያለው ከበደ በበኩላቸው ክልሉ ባለፉት ስምንት ወራት ለ44 ሺህ 893 ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።
ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረትም የበርካቶች ህይወት እየተለወጠ መሆኑን ነው የተናገሩት።
ወደሥራ የሚገቡ ወጣቶችን ለማብቃት ከሚሰጣቸው ስልጠና በተጨማሪ የመስሪያና የመሽጫ ቦታዎች እንዲሁም የብድር አገልግሎት መመቻቸቱን አስረድተዋል።
በሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ የሚሆኑ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ ባለፉት አራት ዓመታት ከ300 ሺህ በላይ ወጣቶች ተጠቃሚ መሆናቸውንና የቁጠባ አቅማቸውም ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተናግረዋል።
ከዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ወጣቶች ተደራጅተው መንግስት ባመቻቸላቸው የብድርና የመስሪያ ቦታ የግንባታ ግብዓት እያመረቱ መሆናቸውን የገለጸው ደግሞ ከይርጋለም ከተማ የመጣው ወጣት ታምራት ካሳ ነው።
ሥራውን በጀመሩ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ካፒታላቸው ከአራት ሚሊዮን በላይ መድረሱንና ለ28 ሰዎች የሥራ እድል መፍጠራቸውን ተናግሯል።
ከምስራቃዊ ሲዳማ ዞን የመጣው ወጣት ብሩክ ቡኖያ በበኩሉ ለአምስት በመደራጀት መንግስት ባመቻቸላቸው የብድር አቅርቦትና የመስሪያ ቦታ ከሦስት ዓመት በፊት ወደሥራ መግባታቸውን ተናግሯል።
በመዝናኛ አገልግሎት ዘርፍ እንደተሰማሩና ካፒታላቸው ወደ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ማደጉን የገለጸው ወጣቱ፣ በቀጣይ ወደ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር መዘጋጀታቸውን ተናግሯል።
በመድረኩ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢየዎች የተውጣጡ ከ1ሺ በላይ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን በወጣቶች ስራ እድል ፈጠራና በሚደረጉ ድጋፎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025