
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2017(ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ ከተማ 154ሺህ 923 ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት እና የስራ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ፕሮግራም በይፋ ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ ጃንጥራር አባይ ፕሮግራሙን በከተማ ደረጃ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት የከተማ ልማት ሴፍትኔት ፕሮግራሙ ለሶስተኛ ዙር በከተማው እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት በተካሄዱ ሁለት ዙር የልማት ሴፍትኔት ፕሮግራሞች ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ዛሬ በተጀመረው ሶስተኛ ዙር የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት እና የስራ ፕሮጀክት ላይ የሚሳተፋ ነዋሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
በአጠቃላይ በፕሮግራሙ 154ሺህ 923 ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተመላክቷል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026