
ሀዋሳ፤ መጋቢት 9/2017(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በበልግ ወቅት ከ520 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን ታቅዶ ዝግጅት እየደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ በዘንድሮ የበልግ እርሻ ከ520 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ ነው።

በዚህም በቆሎ፣ ማሽላ፣ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ ሌሎች የሆርቲካልቸር ሰብሎችን በማልማት ከ52 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ በሁሉም ወቅቶች የግብርና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በሚደረጉ ጥረቶች አርሶ አደሩ በማሳው የሚያሳልፈው ጊዜ እየጨመረና ለውጥ እየታየ መምጣቱንም ተናግረዋል።
በቅድመ በልግ ያሉትን ጊዜያቶች እርጥበትና ያሉ የውሃ አማራጮች በመጠቀም ልማቱን ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በክልሉ በልግን ጨምሮ ለ2017/2018 የምርት ዘመን ጥቅም ላይ የሚውል ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል በለይ የአፈር ማዳበሪያ እየቀረበ ነውም ብለዋል።
አርሶ አደሩ በልማቱ ውጤታማ እንዲሆን ከምርጥ ዘር አቅርቦት በተጨማሪ የተቀናጀ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

በክልሉ የምስራቅ መስቃን ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊና የእርሻ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሁሴን ሙስጠፋ በበኩላቸው በወረዳው በበልግ ከ4 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተከናወነ ነው።
በአሁኑ ወቅትም የመሬት ዝግጅት፣ የግብአት አቅርቦትና የባለሙያ ድጋፍ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

በክልሉ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ነዋሪ አርሶ አደር ኢብራሒም ረዲ እና አርሶ አደር ሰለሞን አስራት በበኩላቸው ለበልግ እርሻ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዶቦና ጎላ ቀበሌ በሦስት ሄክታር መሬት ላይ በበጋ መስኖ ካለሙት አትክልትና ስንዴ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው በአሁኑ ወቅትም መሬቱን ለበልግ እርሻ እያዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ለበልግ አርሻ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር እየቀረባቸው መሆኑን ገልጸው፣ በልማቱ የግብርና ባለሙያን ድጋፍ ተጠቅመው ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን አመልክተዋል።

ከበጋ መስኖ ልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለጹት አርሶ አደር ሰለሞን አስራት በበኩላቸው፣ በበልግ እርሻው ውጤታማ ለመሆን ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በበልግ እርሻ በሦስት ሄክታር መሬት ላይ በቆሎ ለማልማት የእርሻ ስራና መሰል ዘግጅቶችን እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026