መጋቢት 9/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ከ300 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ መከፋፈሉን የክልሉ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ገለጸ።
ኤጀንሲው የ2017/18 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እና ግብይት ላይ ያተኮረ መግለጫ ሰጥቷል።
የክልሉ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ጀማል ከድር በሰጡት መግለጫ በክልሉ ዘንድሮ ከ11 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማደበሪያ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ታቅዷል ብለዋል።
ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።
በእስካሁኑ ሂደትም ለክልሉ ከሚቀርበው የአፈር ማዳበሪያ ከ4 ሚሊዬን ኩንታል በላይ የሚሆነው ወደ አገር ውስጥ መግባቱን ገልጸዋል።
የሚቀርበው የአፈር ማዳበሪያ ለበጋ መስኖ፣ ለበልግና ለመኸር አዝመራ የሚውል ሲሆን እስካሁን ከ300 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ተከፋፍሏል ብለዋል።
የአፈር ማዳበሪያው የወቅቱን የዓለም አቀፍ እና የአገር ውስጥ ገበያ ሁኔታዎች ታሳቢ ያደረገ ተጨማሪ ድጎማ ተደርጎ ለአርሶ አደሩ እየቀረበ መሆኑን አስረድተዋል።
ለዚሁ እንዲያግዝ ዘንድሮ 32 ቢሊየን ብር የክልሉ መንግስት ለአፈር ማዳበሪያ ግዢ ድጎማ ማድረጉንም አስረድተዋል።
የአፈር ማዳበሪያ ግብይትም በዲጂታል ዘዴ ታግዞ የሚከናወን መሆኑን ጠቅሰው አርሶ አደሩም ባለው የእርሻ መሬት መጠን ብቻ ማደበሪያ እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል።
የክልሉ አርሶ አደሮችም ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልጋቸውን የአፈር ማዳበሪያ በጊዜ እንዲገዙ አሳስበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025