አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት ትምህርት የሚሆን የዲጂታል ኢኮኖሚና መሰረተ ልማት እየገነባች መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የፈጠራና ቴክኖሎጂ ክፍል ኃላፊ ማክታር ሳክ(ዶ/ር) ገልጸዋል።
ኃላፊው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአፍሪካ ሀገራት ጠንካራ የዲጂታል ፖሊሲ በመዘርጋት የከተማና ገጠር የቴክኖሎጂ ትስስርን በማስፋፋት በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅባቸዋል።
ኢትዮጵያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ በሰጠችው ትኩረት በስራ ዕድል ፈጠራና በኢንቨስትመንት ፍሰት እመርታዊ ለውጥ እያስመዘገበች እንደምትገኝ ገልጸዋል።
መንግሥት ለዲጂታላይዜሽን በሰጠው ትኩረት የኢንተርኔት መሰረተ ልማት ተደራሽነት በሀገሪቱ በእጅጉ መስፋፋቱን አድንቀዋል።
ጠንካራ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የአሰራር ማዕቀፍ በማዘጋጀት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ማቀላጠፍ እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የበይነ መረብ ግንኙነት ዕድገትም ለአህጉሪቱ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሳካት ወሳኝ በመሆኑ ለአፍሪካውያን ተመጣጣኝ አገልግሎት ማቅረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ በዲጂታል መሰረተ ልማትና ኢኮኖሚ ግንባታ ለአፍሪካውያን ትምህርት የሚሆን ስኬት እያስመዘገበች ነው ብለዋል።
የቴክኖሎጂ ንግድ ልማትና ግብይት ባለሙያ የሆኑት ሰርጌይ ጋስፓርያን በበኩላቸው፤ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት የሀገር ውስጥ ገቢ የመሰብሰብ አቅምን ለማሳደግ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ዲጂታላይዜሽን የፋይናንስ አስተዳደርንና የታክስ የመሰብሰብ ሂደትን በማቀላጠፍ ግልጽነት ያለው የገቢና ወጪ ሥርዓት ለመፍጠር ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያም የአምስት ዓመታት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስትራቴጂ በመቅረጽ ባለፉት ዓመታት ያከናወነቻቸው ተግባራት የሚደነቁ ናቸው ብለዋል።
በቀጣይም ከዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎት ሰጪዎች ጋር በመተባበር የዕውቀትና ክህሎት ሽግግር ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አንስተዋል።
ኢትዮጵያ የመንግስትን የመፈጸም አቅም በማሳደግ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገት በመፍጠር አስደናቂ የልማት እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኗንም ጠቅሰዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025