
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2017(ኢዜአ)፡- የአፍሪካን የባህር እና የመጠጥ ውሃ ሀብቶች ያለውን ቀጣናዊ ትብብር ማጠናከርን ያለመው የአፍሪካ የውቅያኖስ አስተዳደር ስትራቴጂ ወደ ትግበራ ሊገባ መሆኑ ተገለጸ።
ስትራቴጂውን ለማፅደቅ የተዘጋጀ አውደ ጥናት ከነገ ጀምሮ በታንዛንያ ዳሬ ሰላም ይካሄዳል።
ስብሰባውን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም በጋራ በመተባበር ነው።
የአፍሪካ የውቅያኖስ አስተዳደር ስትራቴጂ የአፍሪካን የባህር እና የመጠጥ ውሃ ሀብቶች የሀገራት እና የዘርፉ ተዋንያን ትብብርን ለማጠናከር ያለውን ፋይዳ አስመልክቶ ውይይት እንደሚደረግ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የስትራቴጂው ተቋማዊ ማዕቀፍ፣ የክትትል ስርዓትና የድርጊት መርሃ ግብር ውይይት የሚደረግባቸው ዋነኛ አጀንዳዎች ናቸው።
የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ስትራቴጂውን ከብሄራዊ እቅዶቻቸው ጋር አጣጥመው በሚተገብሩበት ሁኔታ ላይም ይመክራሉ።
የውቅያኖስ አስተዳደር ስትራቴጂው ከአፍሪካ የብሉ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ፣ ከዘላቂ ልማት እና ዓለም አቀፍ ግቦች ጋር ያለው ትስስርም ውይይት ይደረግበታል።
እ.አ.አ በ2023 በአሜሪካ ኒው ዮርክ የተፈረመው ዓለም አቀፍ የባህር ብዝሃ ህይወት ዘላቂ አጠቃቀም ስምምነት (BBNJ Agreement) የትግበራ አፈጻጸም ሌላው የአውደ ጥናቱ የመወያያ አጀንዳ ነው።
የአፍሪካ ሀገራት እ.አ.አ ጁን 2025 በፈረንሳይ ኒስ በሚካሄደው ሶስተኛው የተባበሩት መንግስታት የውቅያኖስ ኮንፍረንስ ላይ ይዘው የሚቀርቡትን የጋራ አቋም ይፋ እንደሚያደርጉም የህብረቱ መረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካ የውቅያኖስ አስተዳደር ስትራቴጂ ለማፅደቅ የሚደረገው አውደ ጥናት እስከ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026