
ደሴ፤መጋቢት 18/2017 (ኢዜአ) ፦አገልግሎቱ የቴክኖሎጂ ምዝገባ ስርዓቱን በማስፋት በዘርፉ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማስተካከል በሚቻልበት ላይ በኮምቦልቻ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በምክክር መድረኩ የአገልግሎቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ሞላ ትዕዛዙ እንደገለጹት ፤ በክልሉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባን ተደራሽ በማድረግ መስሪያ ቤታቸውን የመረጃ ቋት ምንጭ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
በዚህም በክልሉ በሚገኙ 122 ማዕከላት የተጀመረው የቴክኖሎጂ ምዝገባ አሰራር በቅልጥፍና እና ጥራት ባለው የመረጃ ቅብብሎሽ ውጤት ማምጣት መቻሉን ተናግረዋል።
የቴክኖሎጂ ምዝገባው ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ ብልሹና ቀርፋፋ አሰራሮችንና የቅንጀት ክፍተቶችን በማስተካከል በኩል አበረታች ለውጥ አምጥቷል ብለዋል።
ከኢትዮ ቴሌኮም እና ሌሎችም ተቋማት ጋር በመተባበር ወደ ተለያዩ ማዕከላት ለማስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለማስፋት በተደረገ ጥረት ዘንድሮ በ166 ጤና ተቋማት የሞትና ልደት ኩነት ምዝገባ መጀመሩን ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም ባለፉት ስምንት ወራት ከ378 ሺህ በላይ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ መካሄዱን ያመለከቱት አቶ ሞላ በቀሪ ወራት ቴክኖሎጂውን በማስፋት ምዝገባውን በንቅናቄ ለማቀላጠፍ መድረኩ አስፈልጓል ብለዋል።
በደሴ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ወሳኝ ኩነቶች የምዝገባ ቡድን መሪ አቶ ጌታቸው መሀመድ በበኩላቸው፥ በሁሉም ማዕከላት በቴክኖሎጂው የተደገፈ ምዝገባ በመጀመራቸው ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል፡፡
በዚህም ብልሹ አሰራሮችን ከማስቀረት ባለፈ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ማስቻሉን አስረድተዋል።
በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ጽህፈት ቤት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ቡድን መሪ አቶ መንግስቴ ወልደየስ ፤ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ምዝገባን ለማስጀመር ግብዓት የማሟላት ሥራ መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡
በዚህ መድረክ መሳተፋቸውም ቀደም ሲል ከጀመሩ ዞኖችና ወረዳዎች ልምድ መቅሰማቸው ቴክኖሎጂውን ለመተግበር ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
በመድረኩ ላይም የክልል፣ የተለያዩ ዞኖችና የከተማ አስተዳደሮች የዘርፉ አመራር አባላትና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026