አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮ-ቴሌኮም ከመልቲ ቾይዝ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ዲ ኤስ ቲቪ ስትሪም ጥቅል የተባለ አገልግሎት ይፋ አድርጓል።
ስምምነቱ ቀልጣፋ ፈጣንና በየትኛውም ጊዜና ቦታ የላቀ ጥራት ያላቸውን ይዘቶች በተለያዩ ስማርት ስልኮች ማግኘት የሚያስችል ነው።
ጥቅሉ ከድምጽና ኢንተርኔት ግንኙነት በተጨማሪ የተለያዩ ተወዳጅ የስፖርት ቻናሎችን ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ ማየት የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ሀገርኛ ይዘቶችን፣ ዓለም አቀፍ ፊልሞችን፣ ዶክመንተሪዎችንና የተለያዩ ሾዎችን መመልከት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚህ ወቅት ትብብሩ ኢትዮ ቴሌኮም ሁሉንም አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ ለማድረግ እየተጓዘበት ያለውን ርቀት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የመልቲ ቾይስ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ገሊላ ገብረሚካኤል በበኩላቸው ዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል አገልግሎት የተለያዩ አማራጮችን የያዘ ጎጆ ቤተሰብ፣ ሜዳ ፕላስና ፕሪሚየምን ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም ደንበኞች የሚፈልጉትን አገልግሎት መርጠው እንዲጠቀሙ የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025