
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት የኢትዮጵያ ግብርና በታሪክ ትልቅ ድል ያስመዘገበበት መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ።
የግብርና ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኖች ባለፉት 7 ዓመታት በለውጡ መንግስት በተሰሩ ስራዎች የተገኙ ስኬቶች ላይ ‘ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!’ በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የሚኒስቴሩ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፈ ሚኒስትር ዴኤታ እያሱ ኤልያስ (ፕ/ር) ባለፉት ሰባት የለውጥ አመታት እንደ ሀገር በርካታ ውጤቶችና ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል
ከለውጡ በፊት በኢትዮጵያ ላይ የተጋረጠውን የመበታተን አደጋና ስጋት ተቀርፎ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የተደረገበት ቀን እንደነበር አውስተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም በለውጥ ዓመታቱ የኢትዮጵያ ግብርና በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ትልቅ ድል የተመዘገበበት ነው ብለዋል።
በስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራና በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮች የተመዘገቡ ውጤቶች የምግብ ዋስትናን እና ስርዓተ ምግብ፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ግብርና ለመገንባት በሚደረገው ጥረት መሰረት የተጣለበት እንደሆነ አመልክተዋል።
የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በበኩላቸው ባለፉት የለውጡ አመታት በኢኮኖሚው ዘርፍ በግብርና ላይ ብቻ የተንጠለጠለውን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብዝሃ-ዘርፍ ኢኮኖሚ ለማድረግ ከግብርናው ባለፈ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝምና በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ዘርፎች ላይ ውጤት መመዝገቡን አመልክተዋል።
በግብርናው ዘርፍ የመጣው ለውጥ የሚታወስና ብዙ የታሪክ እጥፋቶች የመጣበት መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸው የተገኘውን ድል ለማጽናትና ለማስቀጠል አመራሩና ሰራተኛው በበለጠ ቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባው አሳስበዋል።
በለውጡ ዓመታት የተገኙ ድሎችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም አጠቃላይ በኢኮኖሚውና በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት እንደተደረገበት የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026