
ደሴ፤ መጋቢት 28/2017(ኢዜአ)፡- የ'ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ' የኢንቨስትመንት ጥያቄያቸው ፈጣን ምላሽ እንዲያገኝ ማስቻሉን ኢዜአ ያነጋገራቸው የደሴ ከተማ ባለሃብቶች ገለጹ።
“ኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት“ በሚል መሪ ሀሳብ የደሴ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
ከመድረኩ ተሳታፊ ባለሀብቶች መካከል ወይዘሮ የውብዳር ሞላ እንዳሉት፤ የሚስማር ፋብሪካ ለመገንባት ቦታ ባለማግኘታቸው ተቸግረው ቆይተዋል፡፡
በ'ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ' በመጀመሩ ግን ከሁለት ሺህ 800 ካሬ ሜትር በላይ መሬት በማግኘታቸው በ105 ሚሊዮን ብር ካፒታል በአጭር ጊዜ ግንባታውን አጠናቀው ወደ ምርት ሥራ ገብተዋል።
ለ58 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል።

በሞልና አፓርታማ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩት አቶ አህመድ ኑር ስጦታው በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ችግሮቻችን መፈታት በመቻላችን ፈጥነን ወደ ሥራ መግባት ችለናል ብለዋል፡፡
ከከተማ አስተዳደሩ 500 ካሬ ሜትር መሬት ተቀብለው በአንድ ቢሊዮን ብር ካፒታል ወደ ግንባታ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት ለኢንቨስትመንት ዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ውጤት መመዝገብ ተችሏል ብለዋል፡፡
ቀጣይም በዘርፉ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በማስተካከል በስፋት ተኪ ምርት እንዲመረትና ገበያው መረጋጋት እንዲችል በቅንጅት እንሰራለን ሲሉ ገልጸዋል።
ንቅናቄው በዘርፉ ችግሮች በመፍታት ኢንቨስትመንትን ማነቃቃት መቻሉን የደሴ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ አለባቸው ሰይድ ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ ስምንት የኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች ምርት መግባታቸውን ጠቁመው፤ 36 ፋብሪካዎች ደግሞ በግንባታ ላይ ናቸው ብለዋል።
በጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ26 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 125 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዳወጡ ገልጸዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026