ደሴ፣መጋቢት 30/2017 (ኢዜአ)፡ -እየጣለ ያለው ዝናብ ለበልግ አብቃይ አካባቢዎች ምቹ በመሆኑ አርሶ አደሩ የሰብል ልማቱን ማቀላጠፍ እንዳለበት በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምስራቅ አማራ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል አሳሰበ፡፡
የማዕከሉ የልማት ሚቲዎሮሎጂ ዴስክ ኃላፊ አቶ እንዳላማው ወልዴ ለኢዜአ እንደገለጹት የዘንድሮው የበልግ ዝናብ ፈጥነው ለሚደርሱ ሰብሎች ምቹ ነው።
አርሶ አደሩ በምስራቅ አማራ ዞኖች የሚዘንበውን ቀላልና መካከለኛ ዝናብ ተጠቅሞ ፈጥነው መድረስ የሚችሉ ሰብሎች ላይ በማተኮር የዘር ስራውን ማቀላጠፍ እንዳለበት ገልጸዋል።
ከዚህ ጎን ለጎንም የሚዘንበውን ዝናብ በማሳ ዳር ዳር አቅቦ በማስቀረትና ወደ ግድቦችና ኩሬዎች በማስገባት የዘሩት ሰብል ምርታማ እንዲሆን አልመው መስራት እንደለባቸው አሳስበዋል።
የበልግ ዝናቡ ለሰብል ልማት፣ ለእንሰሳት ግጦሽ፣ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማትም የሚያስገኘው ጠቀሜታ ከፍ ያለ በመሆኑ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።
የበልግ ዝናቡ ደረቅና ሞቃት የአየር ጸባይ ስለሚፈጥር ህብረተሰቡ ከተለያዩ በሽታዎች እራሱን እንዲጠብቅ ያሳሰቡት አቶ እንዳላማው በተለይ የወባ መራቢያ ሥፍራዎችን ማጽዳት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ ይመር ሰይድ በበኩላቸው በዞኑ የበልግ ዝናብን በመጠቀም ከ50 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በተለያየ የሰብል ዘር ተሸፍኗል ብለዋል፡፡
አርሶ አደሩ ያገኘውን እርጥበት ተጠቅሞ ወደ ልማቱ እንዲገባ በየደረጃው ባሉ የግብርና ባለሙያዎች እገዛ እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
በዞኑ ከ104 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበልግ በማልማት ከሁለት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ከዞኑ ግብርና መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025