አሶሳ፤ መጋቢት 30/2017(ኢዜአ):- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በእስካሁኑ እንቅስቃሴ 56 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ገብቶ ስርጭት መጀመሩን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በቢሮው የግብርና ግብዓት አቅርቦት እና የምርት ግብይት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ በቀለ ለኢዜአ እንደገለፁት በምርት ዘመኑ ለክልሉ 231ሺህ 340 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ተመድቧል።
ከዚህ ውስጥም በእስካሁኑ በተደረገ የማጓጓዝ ስራ በአሶሳ እና መተከል ዞን በሚገኙ ማዕከላት 56ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ገብቶ ስርጭት መጀመሩን ገልፀዋል።
አምስት ሺህ ኩንታሉ ደግሞ ለአርሶ አደሩ መሠራጨቱን ዳይሬክተሩ አክለዋል።
የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ መድረስ አርሶ አደሩ የዝናብ ወቅት ከመግባቱ በፊት ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ እና ክረምት ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ምቹ ባልሆኑ አካባቢዎች በጊዜ እንዲደርስ መልካም አጋጣሚ መሆኑንም ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት የግብርና ግብዓት መመሪያ በማዘጋጀት አርሶ አደሩ ማዳበሪያን ያለምንም እንግልት እንዲያገኝ እየተደረገ እንደሆነም ገልፀዋል።
በዚህም አርሶ አደሩ በማሳው ልክ የአፈር ማዳበሪያ እንዲያገኝ እና ከሶስተኛ ወገን ነፃ በሆነ መልኩ እንዲወስድ የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ነው የተናገሩት።
በአሁኑ ወቅት አርሶ አደሩ የአፈር ማዳበሪያ እንዲወስድ የንቅናቄ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው፤ አርሶ አደሩ የእርሻ ወቅት ከመድረሱ በፊት የማዳበሪያ ግዥ በመፈጸም ለእርሻ ማሳቸው ዝግጁ እንዲያደርጉ ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል።
በክልሉ ከአፈር ማዳበሪያ በተጨማሪ የምርጥ ዘር አቅርቦት መኖሩን ተናግረው፥ ከተደለደለው 5ሺህ 292 ኩንታል ውስጥ 800 ኩንታል ገብቶ ስርጭት መጀመሩን ጠቅሰዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025