
ዲላ፤ መጋቢት 30/2017 (ኢዜአ)፡-በዲላ ከተማ አስተዳደር ከ91 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ግንባታ ሥራ ተጀመረ።
በግንባታ ማስጀመሪያው ላይ የከተማው ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ ምንተስኖት ከበደ እንደገለጹት የመሰረተ ልማት መስፋፊያዎቹ ለህዝብ የልማት ጥያቄ ቅድሚያ የሰጡ ናቸው።

በማስፋፊያ ግንባታው ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ መንገድና የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦ፣ ሁለት መለስተኛ ድልድዮችና አንድ ማዕከልን ጨምሮ 25 ፕሮጀክቶች መካተታቸውን አመልክተዋል።
ፕሮጀክቶቹ ለ3 ሺህ 456 ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ የከተማዋን ደረጃ የሚያሳድጉ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ግንባታው በቀጣይ ሦስት ወራት እንደሚጠናቀቅ የገለጹት አቶ ምንተስኖት፣ ለሥራው የሚያስፈልገው ከ91 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ወጪ በዞኑና በከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፈንም ተናግረዋል።
የዲላ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰቡን የብዙ ጊዜ የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ በትኩረት እየሠራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ተወካይ አቶ መንግሥቱ ተክሌ ናቸው።

ዛሬ ግንባታቸው የተጀመሩት የተለያዩ መሰረተ ልማቶች የእዚሁ አካል መሆናቸውን ያስረዱት ሃላፊው፣ የልማት ሥራዎቹ የከተማውን ገጽታና ደረጃ ከማሳደግ ባለፈ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ብለዋል።
ህብረተሰቡ ለልማት ሥራዎቹ ስኬታማነት በተለያየ መንገድ ድጋፍ ከማድረግ ጀምሮ ለተሰሩ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ተገቢ ጥበቃና እንክብካቤ ሊያደርግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ከከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ ደሳለኝ ኮርሜ በበኩላቸው ለዓመታት ሲያነሱት የነበረው የመሠረተ ልማት ጥያቄ ምላሽ እያገኘ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልፀው፣ የግንባታ ሥራው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026