ጋምቤላ፤መጋቢት 30/2017 (ኢዜአ)፦በጋምቤላ ክልል የግብርናውን ልማት በሜካናይዜሽን በመደገፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመሩት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።
በዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ "መርሲ ኮርፕስ"/Mercy Corps/ በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅትና በጋምቤላ ብድርና ቁጠባ ተቋም ትብብር የተገዙ ዘጠኝ የእርሻ ትራክተሮች ለክልሉ ድጋፍ ተደርጓል።
ርዕሰ መስተዳደሯ በርክክቡ ላይ እንዳሉት፥ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማስፋትና ልማቱን በማሳለጥ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ተግተን እንሰራለን።
በተለይም በመጪው የመኸር እርሻ አንድም መሬት ጾም እንዳያድር የግብርና ልማቱን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሯ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም፣መርሲ ኮርፕስ ለተሰኘ ግብር ሰናይ ድርጅት፣ ለክልሉ ብድርና ቁጠባ ተቋምና ለአኝዋሃ ልማት ማህበር ዘርፉን ለማገዝ ላደረጉት ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተደድሩ ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር) በበኩላቸው፥በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመንና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የአጋር አካላት ድጋፋና ትብብር ወሳኝ ነው።
የክልሉ መንግስት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ከተረጂነት ለመላቀቅ ሰፊ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በዓለም ምግብ ፕሮግራም፣መርሲ ኮርፕስ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርድት እና ከክልሉ ብድርና ቁጠባ ተቋም ጋር በመተባበር የክልሉን የግብርና ልማት ለማገዝ ያደረጉት የትራክተር ድጋፍ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን ገልጸዋል።
ትራክተሮቹ የግብርናውን ልማት በማሳለጥ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የጎላ ፋይዳ ይኖራቸዋል ብለዋል።
በዓለም ምግብ ፕሮግራም የጋምቤላ ቅርንጫፍ ተጠሪ ሚስተር ኒክሰን ኡላንግ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ድርጅቱ ድጋፉን ያደረገው በክልሉ እየተካሄደ ያለውን የግብርና ልማት ሽግግር ለማገዝ ነው።
የጋምቤላ ብድርና ቁጠባ ተቋም ስራ አስኪያጅ አቶ ኡቻን ኡቻን በበኩላቸው፥ ድጋፉ ባህላዊ ግብርናን ወደ ዘመናዊ የግብርና ልማት ለማሸጋገር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ጉሊህ ድርሻ አለው ብለዋል።
ትራክተሮቹ በዓለም ምግብ ፕሮግራም፣በመርሲ ኮርፕስና በክልሉ ብድርና ቁጠባ ተቋም ከ145 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገዙ ናቸው ተብሏል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025