የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

አማራጭ የጸሐይ ኃይል ተጠቃሚ መሆናችን ኑሯችንን ለማሻሻልና ለማዘመን አግዞናል

Apr 10, 2025

IDOPRESS

ሚዛን አማን፤ሚያዚያ 1/2017 (ኢዜአ)፦አማራጭ የጸሐይ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸው፥ኑሯቸውን ለማሻሻልና ለማዘመን እያገዛቸው መሆኑን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን የመኤኒት ሻሻ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ።


ከሀገሪቱ ዜጎች 35 በመቶ የሚሆኑት በ2030 በተለያየ የሀይል አማራጭ ተጠቃሚ ለማድረግ ግብ ተይዞ እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል።


በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን በ60 ሚሊዮን ብር የተገነባው የይርኒ የጸሐይ ኃይል ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።


በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑ የወረዳው ነዋሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፥ አማራጭ የጸሐይ ኃይል ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸው ኑሯቸውን በተለያየ መንገድ ለማዘመን እያገዛቸው ነው።


ከነዋሪዎቹ መካከል ወይዘሮ ሀና ደምሴ የሀይል አማራጭ ተጠቃሚ መሆናቸው የቤት ውስጥ የሥራ ጫናን እንዳቃለለላቸው ገልጸዋል።


መንግስት ከጨለማ እንድንወጣ ስላደረገን እናመሰግናለን ያሉት ነዋሪዋ የአካባቢው ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ መሆናቸው ቀደም ሲል ለማገዶ እንጨት ይፈጽሙት የነበረውን የደን ጭፍጨፋ ማስቀረቱን ተናግረዋል።


በወረዳው የይርኒ ቀበሌ ነዋሪ መምህር ዓለሙ ኢሳያስ በበኩላቸው፥ አማራጭ የፀሐይ ኃይል መጠቀም መጀመራቸው ኑሯቸውን ለማዘመን እያገዛቸው መሆኑን ተናግረዋል።


በቤት ውስጥ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሠሩ መሳሪያዎችን ከመጠቀም ባለፈ አማራጭ ሀይልን በመጠቀም ኑሯቸውን የሚያሻሽሉ ተግባራትን ለማከናወን ማቀዳቸውን ገልጸዋል።


በተለይም በአካባቢው የኃይል አማራጭ መዘርጋቱ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ መሳሪያዎች የተደገፉ ትምህርቶችን በተግባር እንዲወስዱ ያስችላል ብለዋል።


ቀደም ሲል በአካባቢያቸው የኃይል አማራጭ ባለመኖሩ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መረጃ ለማግኘት ይቸገሩ እንደነበር የተናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ወይንሸት ወርቁ የተባሉ የወረዳው ነዋሪ ናቸው።


በአካባቢያቸው የተገነባው የይርኒ አማራጭ የጸሐይ ኃይልን መጠቀም መጀመራቸው ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ መረጃዎችን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ለማግኘት እንዳስቻላቸውና ከዘመኑ ጋር ለመራመድ እንዳገዛቸው ተናግረዋል።


ሚኒስቴሩ 35 በመቶ የሚሆኑ ዜጎችን በ2030 የተለያየ የኃይል አማራጭ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ(ዶ/ር) ናቸው።


በምዕራብ ኦሞ ዞን የተመረቀውና ለ5 ሺህ ዜጎች አገልግሎት የሚሰጠው የይርኒ የፀሐይ ሀይል ፕሮጀክት አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ከ65 በመቶ በላይ የሚሆኑ ዜጎችንም የዋናው መስመር ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን አመልክተዋል።


እንደእሳቸው ገለጻ፥ በአሁኑ ወቅት አፈጻጸማቸው ከ50 በመቶ በላይ የሆነና ከ240 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የጸሐይ ኃይል ፕሮጀክቶች በግንባታ ሥራ ላይ ናቸው።


በተጨማሪም 750 ሺህ የቤተሰብ ሶላር እንዲሁም 1 ሺህ 400 የተቋም ሶላሮችን ለማሰራጨት ሥራው በጨረታ ሂደት ላይ ይገኛል ብለዋል።


አማራጭ የኃይል ዝርጋታ ሥራውን ስኬታማ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ከአጋር ድርጅቶችና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025