አዳማ/ ቦንጋ/ አርባምንጭ፤ ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ የሀገር የህልውና መሰረትና የትውልዱ ጥያቄ በመሆኑ ቀና ምላሽ የሚሻ መሆኑን በተለያዩ ከተሞች ኢዜአ ያነጋገራቸው ወጣቶች ገለጹ።
ኢትዮጵያ ከባህር በቅርብ ርቀት ላይ ሆና የባህር በር ተነፍጓት ብትቆይም አሁን ላይ የሀገር የህልውና ጉዳይ እና የትውልዱ ጥያቄ ሆኖ መነሳት ከጀመረ ውሎ አድሯል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ተደጋጋሚ ማብራሪያዎችን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፤ የበዛ ህዝብ ይዘን ተቆልፎብን መኖር ስለማንችል የባህር በር ጉዳይ የህልውና ጥያቄ መሆኑን በተደጋጋሚ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመደመር ትውልድ መፅሃፋቸው ላይም የባህር በር ጉዳይ ምላሽ የሚሻ የትውልዱ ጥያቄ መሆኑን ማስፈራቸው ይታወቃል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ በአዳማ፣ ቦንጋ እና አርባ ምንጭ ከተሞች ያነጋገራቸው ወጣቶች የኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ የሀገር የህልውና መሰረትና የትውልዱ ጥያቄ በመሆኑ ቀና ምላሽ የሚሻ መሆኑን ተናግረዋል።
የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪው ወጣት ተገኝ አበራ፣ የቦንጋ ከተማ ነዋሪው ወጣት አክሊሉ ሀይለማሪም እና የአዳማ ከተማ ነዋሪው ወጣት አቤሜሌክ አየለ፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ ለሀገር የህልውና መሰረት ከመሆኑም በላይ የትውልዱ ጥያቄ በመሆኑ ቀና ምላሽ እንደሚሻ ገልጸዋል።
በዚህ ረገድ መንግስት ጥያቄውን አንስቶ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ አጠናክሮ መቀጠሉን በማድነቅ ለስኬታማነቱ የድርሻችንን ለመወጣት እንሰራለን ሲሉም አረጋግጠዋል።
የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎቹ ወጣት ግሩምነሽ ሀጫ እና ወጣት ቀኝያለው ትዕዛዙ፤ የባህር በር ጥያቄው በሰጥቶ መቀበል መርህ በመንግስት የተጀመረው የዲፕሎማሲ ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
የአሁኑ ትውልድ በመደመር መርህ ብሔራዊ ጥቅምን፣ ሀገራዊ ልማትና እድገትን አንግቦ እየሰራ መሆኑን ያነሱት ወጣቶቹ ቀጣይነት ያለው ጥረት እናደርጋለን ሲሉም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ፍትሃዊነትን ያነገበና የሀገር የህልውና ጉዳይ በመሆኑ የዲፕሎማሲ ጥረቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ መግለጻቸው ይታወሳል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025