መቀሌ፤ሚያዚያ 2/2017( ኢዜአ) ፡-በትግራይ ክልል በበጋ መስኖ በመጀመሪያው ዙር ከለማው መሬት 6 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱ ተገለፀ።
በበጋ መስኖ ልማቱ ከ130 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተሳታፊ መሆናቸውም ተገልጿል።
በጊዜያዊ አስተዳደሩ የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ የመስኖ ልማት ዳይሬክቶሬት የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ቡድን አስተባባሪ አቶ ሀየሎም ተካ ለኢዜአ እንደገለፁት በክልሉ በመጀመሪያው ዙር በመስኖ ከለማው 58 ሺህ ሄክታር መሬት የ54 ሺህ ሄክታሩ የምርት ግምገማ ተጠናቋል።
በክልሉ በበጋ መስኖ ከለማው መሬት አስካሁን በተሰበሰበው መረጃ 6 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን ተናግረዋል።
በበጋ መስኖ የለማው አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ የተለያዩ ሰብሎች እንደሚገኙባቸው የገለፁት አስተባባሪው ሁለተኛው ዙር የበጋ መስኖ ልማት ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል።
የአርሶ አደሩ የመስኖ ልማት ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱን የተናገሩት አስተባባሪው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሰራታቸው፣ የግብዓት አቅርቦትና የባለሙያ ድጋፍ ታክሎበት የተሻለ ምርት ሊገኝ መቻሉን ገልፀዋል።
በዘንድሮው የመጀመሪያ ዙር የመስኖ ልማት ከ130 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን ገልፀው ከዚህም ውስጥ 39 ሺህ 506ቱ ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በመስኖ ልማት የተሳተፉ አርሶ አደሮች ተጠቃሚነት ሌሎች አርሶ አደሮችን ለተሳትፎ ማነሳሳቱንም አስተባባሪው ገልፀዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025