ዲላ፤ሚያዝያ 4/2017 (ኢዜአ) :-የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉባቸውን ማነቆዎች በመፍታት ውጤታማነታቸውን እንዲያረጋግጡ እየተደረገ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ9 ወራት አፈጻጸም ግምገማና የዲላ መካከለኛ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እንቅስቃሴ ጉብኝት ተካሄዷል።
በመድረኩ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሐመድ እንዳሉት፥ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ግብርናን ከማዘመን ባለፈ ወደ ኢንዱስትሪ ለሚደረገው ሽግግር መሰረት ናቸው።
በሀገሪቱ የሚገኙ እነዚህ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርኮች ምርቶች ላይ እሴት ጨምረው የማቀነባበር ሚናቸውን እንዲወጡና ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ የሚገጥማቸውን ማነቆዎች መፍታትን ጨምሮ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ፓርኮቹ በተለይም የፋይናንስ፣ የኃይል አቅርቦትና የገበያ ትስስር ችግሮች መለየታቸውን ገልጸው፥ በተቀናጀ መንገድ በመፍታት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ የሚያስችል ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የዲላና የይርጋጨፌ መካከለኛ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርኮችን በማስተዋወቅ አልሚ ባለሃብቱን በመሳቡ ረገድ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ያነሱት ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ብርሃኑ ናቸው።
ፓርኮቹ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ተከናውኖላቸው ለምርት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰው፥ በተለይ የዲላው ፓርክ የአቮካዶ ዘይት በማምረት በወጪ ንግድና በስራ ፈጠራ ረገድ ውጤታማ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን አመልክተዋል።
በቀጣይ 90 ቀናት ወደ ፓርኩ ለመግባት ፍላጎት ያሳዩ 6 ባለሃብቶችን ስራ በማስጀመር የፓርኩን ውጤታማነት ለማጠናከር ስምምነት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል።
በመድረኩም ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025