
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 4/2017 (ኢዜአ) ፦ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አጠቃላይ አፈጻጸም 98 ነጥብ 66 በመቶ መድረሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የአፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ማካሄድ ጀምረዋል።
መርሃ ግብሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም አቅርቦትን በመመልከት የጀመረ ሲሆን ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያ በሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ላይ ያለው ተፅዕኖ አጠቃላይ ምልከታ ቀርቧል።
በመካሄድ ላይ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም እርምጃ ወቅታዊ መረጃ መቅረቡንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የዓለም ኢኮኖሚ በ2025 በ3 ነጥብ 3 በመቶ የሚያድግ መሆኑ የተተነበየ መሆኑም የተገለጠ ሲሆን ከሰሃራ በታች ያለውን የአፍሪካ ክፍል ጨምሮ አብዛኛው የዓለም ክፍል አዎንታዊ እድገት እንደሚያስመዘግብ ተገልጧል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 8.4 በመቶ እንደሚያድግ መተንበዩን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም መርሃ ግብር የተረጋጋ ሆኖ የቁጠባ እና የኢንቨስትመንት እድገትም አሳይቷል።
የውጭ እዳ ከሀገራዊ የምርት መጠን(ጂዲፒ) ያለው ምጣኔ 13 ነጥብ 7 ከመቶ በመድረስ ትርጉም ባለው መጠን መቀነሱ ተገልጿል።
በተጨማሪም አዲስ የውጭ ምንዛሬ አሰራር መዘርጋቱም ከውጭ የሚላክ የውጭ ምንዛሪ እንዲጨምር በማድረግ የኢትዮጵያን የውጪ ምንዛሬ ክምችት መጨመሩም እንዲሁ።
ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም ከግብርና፣ ከማዕድን፣ ከኢንደስትሪ እና ኤሌክትሪክ የተገኙ የውጭ ንግድ ገቢዎችም እድገት ማሳየታቸው በግምገማው ወቅት ተገልጿል።
ቡና፣ ወርቅ፣ ጥራጥሬ፣ የዘይት ምንጭ ፍሬዎች፣ አበባ እና ኤሌክትሪክ አምስቱ ቀዳሚ የውጭ ንግድ ምርቶች መሆናቸውም ተጠቁሟል።
በሌላ በኩል ግምገማው ታላላቅ የመሠረተ ልማት እና ሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶችንም አፈፃፀም ተመልክቷል።
ለአብነትም የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ 98 ነጥብ 66 ከመቶ አፈፃፀም ላይ የደረሰ ሲሆን ስድስት ዩኒቶቹም ወደ ስራ መግባታቸው የጽህፈት ቤቱ መረጃ ያሳያል።
ዛሬ ጠዋት የነበረው ግምገማ የዘላቂ የልማት ጥረቶች በተለይም አካታችነትን እንደ ቁልፍ የስኬት መለኪያ በመውስድ በመመልከት ተጠናቋል።
ለዘላቂ ልማት ሥራ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ የሥራ ተግባራትም መቅረባቸው ተመላክቷል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026