የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በመዲናዋ በኢንዱስትሪ ዘርፉ የተገኙ ውጤታማ ስራዎችን ለማጠናከር እየተሰራ ነው - ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ

Apr 14, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 4/2017 (ኢዜአ) ፦በኢንዱስትሪ ዘርፉ የተገኙ ውጤታማ ስራዎችን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡

በአዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ከመጋቢት 29 ጀምሮ "ከሸማችነት ወደ አምራችነት" በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ - አዲስ አበባ ታምርት የ2017 ዓ.ም የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ-ርዕይ ተጠናቋል፡፡

በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ ከጥቃቅንና አነስተኛ ወደ አነስተኛ፣ ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ እና ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ የደረጃ ሽግግር ላደረጉ አምራቾች እና በከተማዋ ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች እውቅና ተሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጃንጥራር አባይ በዚሁ ወቅት፤ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጠራና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ጉልህ ሚና በማበርከት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከ3 ሺህ 700 በላይ ኢንዱስሪዎች መኖራቸውን ያነሱት ምክትል ከንቲባው የማምረት አቅማቸው ከ64 በመቶ ላይ መድረሱን ጠቅሰዋል።

ኢንዱስትሪዎቹ ተኪ ምርትና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማምረት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የኢንዱስትሪዎቹን የማምረት አቅም ለማሳደግና ለዘርፉ መነቃቃት የሚያግዝ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ስራ መገባቱን አንስተዋል።

በአውደርዕዩ የገበያ ትስስርና ምርትን የማስተዋወቅ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመው መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች ባዛርና አውደርዕይ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን ይበልጥ ለማላቅ መሥራት እንዳለባቸው የገለጹት ምክትል ከንቲባው፥ የከተማ አስተዳደሩ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

በመዲናዋ በኢንዱስትሪ ዘርፉ የተገኙ ውጤታማ ስራዎችን ዘላቂ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ በወጪ ንግድ፣ተኪ ምርቶችን በማምረት፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በሌሎች መስፈርቶች ለተሻሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች እውቅና ተሰጥቷል፡፡

የዘናጭ ማኑፋክቸሪንግ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ተስፋዬ አባቴነህ፥ በሰሩት ስራ እውቅና ማግኘታቸውን ጠቁመው ድርጅቱ ተኪ ምርቶችን ከማምረት አኳያ አመርቂ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የተሰጣቸው እውቅና ድርብ ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ድርጅታቸውን በማስፋፋት ተጨማሪ ስራ ዕድሎችን ለመፍጠር መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

የብራስ ጋርመንት ተወካይ ሳምራዊት ንጉስ በበኩሏ፥ ድርጅታቸው በጨርቃጨርቅ ዘርፍ ከ300 በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡

ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ አምራችነት የተሸጋገሩት የሉሲያን ኮንስትራክሽን የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ መሠረት አበበ፤ የደረጃ ሽግግሩ ከበርካታ ውጣውርዶች በኋላ የተገኘ መሆኑን ጠቅሰው ለላቀ ስኬት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ወደ መካከለኛ አምራችነት የተሸጋገሩት የኃይለሥላሴ እና ጓደኞቹ የድንጋይ ቅርጻቅርጽ ስራ ሕብረት ማህበር ስራ አስኪያጅ ኃይለ ሥላሴ ጣሰው፥ እውቅናው የተሻለ ምርት ለማምረትና ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚረዳቸው ገልጸዋል፡፡

የማርታ ሳምሶንና ጓደኞቻቸው የድንጋይ ቅርጻቅርጽ ሽርክና ማህበር ስራ አስኪያጅ ማርታ ታለጌታ በበኩላቸው ድርጅታቸው፥ ወደ መካከለኛ አምራችነት ማደጉን ጠቅሰው፥ ለምርት ጥራትና ተወዳዳሪነት እንደሚተጉ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025