የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ማዕከሉ በእንሰት ዝርያ ምርምር፣ በበሽታ መከላከልና በቴክኖሎጂ ስርጸት ስኬታማ ሥራ እያከናወነ ነው

Apr 14, 2025

IDOPRESS

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዚያ 5/2017(ኢዜአ)፦ የአረካ ግብርና ምርምር ማዕከል በእንሰት ዝርያ ምርምር፣ በበሽታ መከላከልና በቴክኖሎጂ ስርጸት ስኬታማ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ።

ማዕከሉ 37 ሺህ የእንሰት ችግኞችን ለተለያዩ ክልሎች ማሰራጨቱም ተመላክቷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን የሚገኘው የአረካ ግብርና ምርምር ማዕከል በሰብል፣ በእንስሳትና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የተለያዩ ችግር ፈቺ ምርምሮችን ከማድረግ ጎን ለጎን ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅና በማስረጽ በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ሥርአት አሻራውን እያኖረ ይገኛል።


የማዕከሉ ዳይሬክተር ገነነ ገዛኸኝ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት ማዕከሉ በግብርናው ዘርፍ በሚያካሂደው ጥናት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለፖሊሲ ግብአት የሚሆኑ የምርምር ሀሳቦችን ያቀርባል።

የቴክኖሎጂ ሽግግርና ተግባቦትን ለማጠናከር በሠርቶ ማሳያዎች እና በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ማህበረሰብ አቀፍ ሥራን አጠናክሮ እያከናወነ መሆኑንም ነው ያመለከቱት።

በተለይ በእንሰት ዝርያ ምርምር፣ በበሽታ መከላከል እና በቴክኖሎጂ ስርጸት የተሳካ ሥራ እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም በስድስት ሄክታር መሬት ላይ በምርታማነታቸው፣ በሽታን በመቋቋምና ቶሎ በመድረስ የተሻሉ ስድስት የእንሰት ዝርያዎችን ብዜትና ምርምር ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን ገልጽዋል።

በቅርቡ ውጤታማነታቸው የተረጋገጡ 37 ሺህ የእንሰት ችግኞችን ለተለያዩ ክልሎች ማሰራጩቱን ጠቁመው፣ በተጨማሪም ከ8 ሺህ በላይ ችግኞችን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ ዞኖች ለማሰራጨት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ማዕከሉ ጅማ፣ ቆሎምሶ እና ወንዶ ገነትን ጨምሮ ከስምንት የግብርና ምርምር ማዕከላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

እንሰት ድርቅን በመቋቋምና በንጥረ ነገር ይዘቱ የተለየ በመሆኑ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና አለው ያሉት ዳይሬክተሩ እንሰት እንዲስፋፋ ማዕከሉ የሚጠበቅበትን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።


የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ታምሩ መለኮ በበኩላቸው ማዕከሉ እያከናወነ ያለው ተግባር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት ያግዛል ብለዋል።

ቶሎ በመድረስና በምርት ይዘታቸው የተሻሉ እንደሆኑ በምርምር የተረጋገጡ የእንሰት አይነቶች ለአርሶ አደሩ ከማሠራጨት ባለፈ ለወጣቱ የሥራ ዕድል መፍጠሪያን እያገዙ መሆኑን ተናግረዋል።

የግብርና መምሪያው ከእንሰት ባለፈ በሌሎች ሰብሎች፣ በእንስሳትና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማጉላት ከማዕከሉ ጋር የጀመረውን ቅንጅታዊ አሠራር አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም አስታውቀዋል።


ከአረካ ግብርና ምርምር ማዕከል ቀደም ሲል 250 የእንሰት ችግኞችን እንዳገኙ የተናገሩት ደግሞ የአረካ ዱቦ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ማንዶዬ ማኖ ናቸው።

በምርምር የተገኙት የእንሰት አይነቶች በአካባቢው በተለምዶ ሲጠቀሙባቸው ከነበረው የእንሰት አይነቶች በምርታማነትና በሽታ በመቋቋም ረገድ የጎላ ልዩነት እንዳላቸው አመክተዋል።

እንሰት ለአካባቢው ማህበረሰብ ከምግብ ፊጆታ እስከ ገቢ ምንጭነት እንዲሁም የመሬትን እርጥበት በመጠበቅ ለእርሻና ለከብቶች መኖነት ያለው ዘርፈ ብዙ ጥቅም የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

በመሆኑም ማዕከሉ በዘርፉ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025