አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 5/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ 2 ሪጅን የሰመራ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን አቅም ማሳደግ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የጣቢያው ኃላፊ አስታወቁ።
የጣቢያውን የኦፕሬሽን አቅም ለማሳደግ በባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች የዘመናዊ መቆጣጠሪያ ብሬከር ቅየራ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ኃላፊው አቶ እንድሪስ አህመድ ገልጸዋል።
በማከፋፈያ ጣቢያው ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውን ኤር ኢንሱሌትድ ስዊች ጊር ወደ ጋዝ ኢንሱሌትድ ስዊች ጊር ብሬከር የመቀየር ሥራ መሰራቱ የጣቢያውን የኦፕሬሽን አቅም ማሳደግ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
የብሬከር ቅየራው አሁን ላይ 70 በመቶ መድረሱንና ሲጠናቀቅ የጣቢያውን ኃይል የማቅረብ አቅም አስተማማኝና የተቀላጠፈ እንደሚያደርገውም መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የሰመራ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የዘመናዊ መቆጣጠሪያ ብሬከር ቅየራ ለሰመራ፣ ለሎጊያ፣ ለሚሌ፣ ለአሳይታ፣ ለዱብቲ ከተሞችና ለኢንዱስትሪ ፓርኮች አስተማማኝ ኃይል ማቅረብ ያስችላል ያሉት ደግሞ የሪጅኑ ጥገና ክፍል ኃላፊ አቶ ሙሀመድ አብዱ ናቸው።
የሰመራ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ከኮምቦልቻ በ230 ኪሎ ቮልት የተቀበለውን ኃይል ወደ አፍዴራና ዲቾቶ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በማስተላለፍ ከ80 በመቶ በላይ የሆነውን የአፋር ክልል ተደራሽ ያደርጋል ብለዋል።
አንድ ገቢ መስመርና ሁለት ወጪ መስመሮች ያሉት የሰመራ ማከፋፈያ ጣቢያ በ2003 ዓ.ም ተገንብቶ ለክልሉ በዋነኛነት ኃይል በማቅረብ እያገለገለ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025