የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የቡናና ቅመማቅመም አመራረት ፓኬጆችን በማሻሻል የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማሳደግ ትኩረት ተደርጓል

Apr 15, 2025

IDOPRESS

ሚዛን አማን፣ ሚያዚያ 6/2017 (ኢዜአ):- የቡናና ቅመማም አመራረት ፓኬጆችን በማሻሻል የዘርፉን አኮኖሚያዊ አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ከምርምር ማዕከላት ጋር በመተባበር የተሻሻሉ የቡናና ቅመማ ቅመም ፓኬጆች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች፣ ጋምቤላ እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ለተወጣጡ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች በሚዛን አማን ከተማ እየሰጠ ነው።

ስልጠናው የዘርፉ ባለሙያዎች የቡናን ምርታማነት በጥራት ለማከናወን የተቀረጹ ፓኬጆች ላይ በቂ ግንዛቤ በመያዝ አርሶ አደሩን እንዲደግፉ ያለመ ነው ብለዋል።


በባለሥልጣኑ የሻይና ቡና ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ደፈረስ እንዳሉት ኢትዮጵያ ለቡናና ቅመማ ቅመም ያላትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ ጠንክሮ መሥራት ያስፈልጋል።

ለዚህም ባለሥልጣኑ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ፓኬጆችን በመንደፍ ለአርሶ አደሩ የማስተዋወቅ ተግባር እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የዘርፉን ባለሙያዎች ክህሎት ለማሳደግ በተለያዩ ጊዜያት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን አንስተው የአሁኑም ስልጠና የዚሁ አካል መሆኑን አመልክተዋል።

የአርሶ አደሩን ምርታማነትን ማሳደግ የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሠረት እንደሚጥልም ጠቁመዋል።


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አሥራት መኩሪያ ክልሉ ለቡና ልማት ያለውን ተስማሚነት በመጠቀም ሽፋኑን ለማሳደግ እየሠራ ነው ብለዋል።

በክልሉ ከ582 ሺህ ሄክታር በላይ የቡና ማሳ መኖሩን ጠቅሰው የግብይት ምጣኔን ከፍ ለማድረግ የባለ ልዩ ጣዕም ቡናናን የጥራት ደረጃ ለማሻሻል ትኩረት መደረጉን ገልጸዋል።

ከቡና ባሻገር ከ90 ሺህ ሄክታር በላይ ቅመማ ቅመምና ከ2 ሺህ 300 ሄክታር በላይ የሻይ ልማት መኖሩን ጠቅሰዋል።


የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና ግብርና ቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ ዮሐንስ መላኩ በበኩላቸው በቡና ምርታማነትና ጥራት ላይ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ሊያደርጉን የሚችሉ አስፈላጊ የአመራረት ማሻሻያ ሥራዎችን ለአርሶ አደሩ ማቅረብ ይገባል ብለዋል።

ምርታማነቱንም በሄክታር ያለውን ልዩነት ወጥ በሆነ የአመራረት ዘዴ ለማጥበብ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

ክልሉ ከቡና ባሻገር ለቁንዶ በርበሬ፣ ኮረሪማ፣ ዝንጅብልና ሌሎች የቅመማ ቅመም ምርቶች ምቹ ሥነ ምህዳር ያለው በመሆኑ ተጨባጭ ውጤት ከዘርፉ ለማምጣት ይሠራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025