የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በባህር ዳር ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ከተማዋን በሁለንተናዊ መልኩ እየለወጠ በመሆኑ ተግባሩ ይጠናከራል - አስተዳደሩ

Apr 18, 2025

IDOPRESS

ባህርዳር፤ ሚያዚያ 9/2017(ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ከፍ ያደረገ በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ገለፁ።

በከተማው ከአልማ እስከ ዋተር ፍሮንት ሆቴል የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የ800 ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ዛሬ ተከናውኗል።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አቶ ጎሹ እንዳላማው እንዳሉት በባህርዳር ከተማ በፍጥነትና በጥራት እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማዋን የተፈጥሮ ውበት ይበልጥ አጉልቶ ያወጣ ነው።

በከተማው 22 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የአስፋልት መንገድ ግንባታ እየተከናወነ ሲሆን እስካሁንም 18 ኪሎ ሜትሩን ማጠናቀቅ መቻሉን ገልፀው በቅርቡም ሙሉ ለሙሉ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።


የኮሪደር ልማቱ የብስክሌት፣ የእግረኛ መንገድና የአረንጓዴ ልማትን በማካተት እየተከናወነ ሲሆን ስማርት የባህር ዳር ከተማን ታሳቢ ያደረጉ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነም አመልክተዋል።

የከተማውን ደህንነት በዘላቂነት ለመጠበቅም ከ1 እስከ 10 ኪሎ ሜትር መቅረፅ የሚያስችሉ 468 የደህንነት ካሜራዎችን ለመግጠም ታሳቢ ተደርጎ እየተከናወነ መሆኑንና እስካሁንም 75 ካሜራዎችን ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።

እንዲሁም በከተማው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታትና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

ለዚህም የከተማውን መሬት ለታለመለት ዓላማ ብቻ በዘመናዊ መንገድ ጥቅም ላይ ለማዋል በስድስት ክፍለ ከተሞች የካዳስተር ስራ ከመስራት ባሻገር 56 ሺህ ፋይሎች ወደ ሲስተም መግባታቸውን ገልፀዋል።


የመንገዱ ግንባታ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል አካል እንደሆነም ጠቅሰዋል።

መንገዱ መጪውን ትውልድ ታሳቢ ተደርጎ የሚገነባና የከተማዋን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የበለጠ እንዲጎለብት የሚያግዝ እንደሆነም አብራርተዋል።

በመንገዱ ግንባታ ለተነሱ ግለሰቦችም የመኖሪያ ቤት መገንቢያና ለንግድ የሚሆን ቦታ መሰጠቱን ጠቅሰው ነዋሪዎቹ ለልማቱ መሳለጥ ላደረጉት ቀና ትብብር አመስግነዋል።

በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፣ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር) እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩና የክልል አመራር አባላትና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025