
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 10/2017(ኢዜአ)፦ ኮሪደር ልማትና ተያያዥ ግንባታዎች ከከተሞች የወደፊት ዕድገት ጋር የተሳሳሩ ናቸው ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ልማት አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሃላፊው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ዛሬ ከክልላችን አመራሮች፣ ከሰሜን ሸዋ ዞን እና ከደብረብርሃን ከተማ አመራሮች ጋር በመሆን በደብረ ብርሃን ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራና ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት የመስክ ምልከታ አድርገናል ብለዋል።

በደብረ ብርሃን ከተማ የኮሪደር ልማት መጀመሪያው ምዕራፍ ከጠባሴ መሳለሚያ እስከ በሬሳ ድልድይ ድረስ የ3 ኪሜ ግንባታ መሆኑን ገልጸው ይህም የመንገድ፣ የብስክሌት እና የእግረኛ መንገድን እንዲሁም መናፈሻዎችን ያካተተ ነው ብለዋል።
በተቀናጀ የአመራር ክትትል የመጀመሪያውን ምዕራፍ ቀሪ ስራዎችን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማት ደብረ ብርሃን ከተማን ውብ ገጽታ በማላበስ ለኑሮ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹነቷን የሚያሳድግ እንደሚሆን ገልጸው በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደርና በክልሉ መንግስት ትብብር እየተከናወነ ያለውን ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ግንባታ ሂደት መመልከታቸውን ጠቁመዋል።
የገበያ ማዕከሉ በተጀመረበት የግንባታ ጥራት አግባብ በያዝነው ዓመት ቀሪ ወራት ሲጠናቀቅ አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የገበያ ዋጋን በዘላቂነት ለማረጋጋት ያስችላል ያሉት አሕመዲን መሐመድ(ዶ/ር) የማዕከሉ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆንም ተገቢውን ድጋፍና ክትትል አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026