አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 14/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሁለተኛ ዙር የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ሥልጠና የወሰዱ 127 ሠልጣኞችን አስመርቋል።
በምረቃ መርሃግብሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር)፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እና የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ ተገኝተዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት መንግስት የዲጂታላይዝ አገልግሎት አሰጣጥን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ነው።
በቴክኖሎጂ ክህሎት የዳበረ የሰው ሃይል ማፍራት አገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ንቅናቄ አይተኬ ሚና አለው ብለዋል።
ተቋማትም ይህን በመገንዘብ ሰራተኞቻቸው ሥልጠናውን እንዲወስዱ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ከተማ አስተዳደሩ የዲጂታል አስተዳደር እየዘረጋ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ሂደት የሰው ሃይል ማፍራት ወሳኝ በመሆኑ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና የሰው ሃይል በማፍራት በኩል አይተኬ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።
የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ ተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊና ተደራሽ ለማድረግ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ሥልጠና ብቁ የሰው ሃይል ለማፍራት የተሻለ በመሆኑ እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ የኤጀንሲው ሰራተኞች ሥልጠናውን እየወሰዱ ነው ብለዋል።
ከተመራቂዎች መካከል ወንድማገኝ ሀብታሙ እና ጌትነት ይታየው ሥልጠናው የተለያዩ የቴክኖሎጂ እውቀቶች ማዳበር እንዳስቻላቸው ጠቁመው ይህም የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት ያስችለናል ነው ያሉት።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025