
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2017 (ኢዜአ)፡-በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡና የስራ ባህልን የቀየሩ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተጠሪ ተቋማት እና የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ገለጹ።
የልማት ሥራዎቹ የመዲናዋን ገፅታና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተጠሪ ተቋማት እና የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በዚህም በኮሪደር ልማት፣በመልሶ ማልማት፣በወንዝ ዳርቻ፣ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል፣ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እንዲሁም ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የተሳተፉት የፌዴራል ስነምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን የህዝብ ግንዛቤ ማጎልበቻ መሪ ስራ አስፈጻሚ ነጅመዲን መሐመድ (ዶ/ር) ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት እየተከናወኑ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።
ከዚህም ባሻገር ቀን ከሌሊት ፕሮጀክቶችን በመፈጸም የሥራ ባህል ለውጥ መምጣቱን የጠቀሱት ዶክተር ነጅመዲን፥ የልማት ስራዎቹ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው ብለዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዚዳንት አባንግ ኩመዳን፥ በሁሉም ዘርፎች እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በመዲናዋ ምቹ የመኖሪያ፣ የመዝናኛና የሥራ ከባቢ እየፈጠሩ መሆኑን ተናግራለች።
ከዚህም ባለፈ የከተማዋን ዕድገት የሚያፋጥኑ እንዲሁም የተቀናጁ መሠረተ ልማቶችን ያካተቱ መሆናቸውም የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የብቃትና የሰው ሃብት መሪ ስራ አስፈፃሚ ገዛኸኝ መጎ በበኩላቸው፥ የልማት ስራዎቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ መጠናቀቃቸው የፕሮጀክት የመፈጸም አቅም እያደገ ለመምጣቱ ሁነኛ ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡
በከተማዋ የኮሪደር ልማትና ሌሎች ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባን ገፅታ እየቀየሩ መሆኑን እንደተመለከቱም ጠቅሰዋል።
የልማት ሥራዎቹ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ግብ እንደሚሳካ ተጨባጭ ማሳያ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር የአስተዳደር ዘርፍ አማካሪ ሙሉጌታ ሰይፈ ናቸው።
አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም፥ በአዲስ አበባ በከተማ ግብርና ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
የልማት ስራዎቹ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን በማንሳት በፕሮጀክቶቹ ውስጥ በርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ገልጸዋል።
ህብረተሰቡም ለልማት ስራዎቹ ስኬታማነት እያደረገ የሚገኘውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...
Jun 9, 2026
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...
Jun 6, 2026
ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያ...
May 28, 2026